The Covenant of Mercy | ኪዳነ ምሕረት | 76 Y.O. Ethiopian Christian Gives Birth to Her 1st Child | Miracle of Mary
- Abraham Enoch
- Feb 22
- 7 min read
https://rumble.com/v6o0opf-the-covenant-of-mercy-76-y.o.-ethiopian-christian-gives-birth-to-her-1st-ch.html
😇 ኪዳነ ምህረት | ተዓምረ ማርያም | ፯፮/76 አመቷ ኢትዮጵያዊቷ ክርስቲያን እናት የመጀመሪያ ልጃቸውን በመቐለ ወለዱ
♀️ የ ፯፮/76 ዓመቷ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ የሆኑት ሴት በሰሜን ኢትዮጵያ የትግራይ ክፍለሃገር ዋና ከተማ በሆነችው መቐለ ነዋሪ የሆኑት እምቤይቴ መድህን ሀጎስ (መድህን ባርካ) የተባሉት እናት ለመጀመሪያ ጊዜ ወንድ ልጅ ወለዱ፣ እናታችን ድንግል ማርያም እንዲህ ማረቻቸው። ድንቅ ተዓምር ነው። ይህም ብዙዎችን በማስገረም ላይ ይገኛል።
እንኳን ማርያም ማረችዎ፤ የእኔ እናት! ለእግዚአብሔር የሚሳነው አለ ወይ?!
♀️ 76-Year-Old Orthodox Christian Woman Gives Birth in Tigray-Ethiopia, Sparking Sense of Miracle. A 76-year-old woman, Embeyte Medhin Hagos (aka Medhin Barka) from Mekelle, the capital of the Tigray regional state in northern Ethiopia, has given birth to a baby boy for the first time. It surprises many.
😇 “ኪዳን” የሚለው ቃል "ተካየደ – ተዋዋለ፤ ቃል ኪዳን ተጋባ፤ ተማማለ" ከሚለው የግእዝ ግስ የተገኘ ሲኾን፣ ትርጕሙም ኪዳን፣ ውል፣ መሐላ፣ ቃል ኪዳን፣ የውል ቃል ማለት ነው /ዘዳ.፳፱፥፩፤ ኤር.፴፩፥፴፩-፴፫፤ መዝ.፹፰፥፫/፡፡ በሌላ በኩል ኪዳን የጸሎት ስም ሲኾን፣ ጌታችን ሞትን ድል አድርጎ ከተነሣ በኋላ፣ ከማረጉ በፊት ለሐዋርያት ያስተማራቸው ጸሎት ኪዳን ይባላል፡፡ እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከልጇ ከወዳጇ ከጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የምሕረት ቃል ኪዳን (ውል፣ ስምምነት) የተቀበለችበት ዕለት (የክብረ በዓል ስም) ደግሞ ኪዳነ ምሕረት ይባላል፡፡
በየዓመቱ የካቲት ፲፮ ቀን የምናከብረው ይህ በዓል እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም በጎልጎታ በልጇ በመቃብር ላይ ኾና “ኦ ወልድየ ወፍቁርየ እስእለከ በእንተ ዘተሰባእከ እምኔየ ወበማኅፀንየ ዘጾረተከ፤ ልጄ ወዳጃ ሆይ ከሥጋዬ ሥጋ፣ ከነፍሴ ነፍስ ነሥተህ ሰው ስለመኾንህ፤ ዘጠኝ ወር ከአምስት ቀን ስለቻለችህ ማኅፀኔ፤ ከአንተ ጋር ከአገር ወደ አገር ስለመሰደዴ መጥተህ ልመናዬን ትሰማኝ ዘንድ እለምንሃለሁ” እያለች ስትጸልይ ጌታ እልፍ አእላፍ መላእክቱን አስከትሎ ወደእርሷ መጥቶ ”ሰላም ለኪ ማርያም እምየ፤ እናቴ ማርያም ሰላም ላንቺ ይኹን! እንዳደርግልሽ የምትለምኚኝ ምንድን ነው?” አላት፡፡ እመቤታችንም በስሟ የሚማጸኑትንና መታሰቢያዋን የሚያደርጉትን፣ ለችግረኛ የሚራሩትን፣ ቤተ ክርስቲያን የሚያንጹትን፤ ዕጣን ዘይትና መብአ ለቤተ ክርስቲያን የሚሰጡትን፤ ለእመቤታችንና ለሃይማኖታቸው ካላቸው ፍቅር የተነሣ ልጆቻቸውን በስሟ የሰየሙትን ዅሉ እንዲምርላትና ከሞተ ነፍስ እንዲያድንላት ጠየቀችው፡፡
ጌታችንም “ይህን ዅሉ እንዳደርግልሽ መሐልኩ ለኪ በርእስየ ወበአቡየ ወበመንፈስ ቅዱስ ሕያው፤ በራሴ፣ በአባቴ እና በመንፈስ ቅዱስ ማልኩልሽ” ብሎ ቃል ኪዳን ገብቶላት ወደ ሰማይ ዐርጓል፡፡ ለዚህም ነው ቅዱስ ያዕቆብ ዘሥሩግ በቅዳሴው “… ዳግመኛም በእናትህ በማርያም ተማፅነናል፤ ይህችውም አንተን በመውለድ እመቤታችንና የባሕርያችን መመኪያ ናት፡፡ አንተ “መታሰቢያሽን ያደረገ፣ ስምሽንም የጠራ፣ የዘለዓለም ድኅነትን ይድናል› ብለሃታልና …፤” በማለት የሚማጸነው፡፡
በተአምረ ማርያም መጽሐፍ እንደተመዘገበው በዚህ ዕለት የሚታሰቡ ሁለት ተአምራት አሉ፤ ከእነዚህም አንደኛው የስምዖን ታሪክ ነው፡፡ ስምዖን የሚባል እንግዳ ተቀባይ ደግ ሰው ነበር፡፡ ሰይጣን ለምቀኝነት አያፍርምና ከዕለታት አንድ ቀን በእንግድነት ከቤቱ ገብቶ ”ልጅህን አርደህ ካላበላኸኝ ሌላ ምግብ አልበላም” አለው,።በዚህ ጊዜ ስምዖን ሲያወጣና ሲያወርድ ቆየና “አብርሃም ልጁን ሰውቶ ነው የእግዚአብሔር ሰው የተባለው" በማለት፣ “የእግዚአብሔርን እንግዳ” ላለማሳዘን ሲል ልጁን አርዶ አቀረበለት፡፡ እንግዳ መሰሉ ሰይጣንም ሥጋውን ቅመስልኝ ብሎ ግድ አለው፡፡ ስምዖንም (በላዔ ሰብእ) አርዶ ያዘጋጀውን የልጁን ሥጋ በቀምሰ ጊዜ ሰይጣን ስላደረበት (ስለተዋሐደው) ከዚያች ሰዓት ጀምሮ ቤተሰቦቹን፣ ጎረቤቶቹንና መንገደኛውን ዅሉ ይበላ ጀመር፡፡ በአጠቃላይ ፸፰ ሰዎችን ከበላ በኋላ አንድ በቍስል የተመታ ሰው አገኘና ሊበላው ሲል “ውኃ አጠጣኝ” ብሎ በሥላሴ፣ በቅዱስ ሚካኤል፣ በቅዱስ ገብርኤል ስም ለመነው፤ እርሱም ዝም አለው፡፡
በመጨረሻም "በድንግል ማርያም ስም" አለው፡፡ ስምዖን የእመቤታችንን ስም በሰማ ጊዜም ወደ ልቡናው ተመልሶ “እስኪ ቃሉን ድገመው" አለው፤ በሽተኛውም መልሶ "ስለ ድንግል ማርያም ውኃ አጠጣኝ” ብሎ ለመነው፡፡ ያን ጊዜ “ይህችስ እንደምታስምር በልጅነቴ ሰምቻለሁ” ብሎ ጥቂት ውኃ ሰጠው፤ ውኃው ጕሮሮውን እንኳን ሳያርስለት “ጨረስህብኝ” ብሎ ነጥቆት ሔደ፡፡ በሌላ ቦታም አንድ ገበሬ አግኝቶ ሊበላ ሲል ገበሬው “በላዔ ሰብ የምትባል አንተ ነህ?” ባለው ጊዜ “ለካስ አመሌን ሰው ዅሉ አውቆብኛል” ብሎ ዋሻ ገብቶ በመጸጸት በዚያው ሞተ፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ጽልመት መጥተው ሲወስዷት እመቤታችን “ልጄ በማይታበል ቃልህ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?” አለችው፡፡ ጌታችንም “ሰባ ስምንት ነፍስ ያጠፋ፣ ፈጣሪውን የካደ ሰው ይማራልን?” አላት፡፡ እመቤታችንም “በስሜ የተጠማውን ውኃ አጥጥቶ የለምን?” ብላ ስምዖንን (በላዔ ሰብእን) አስምራዋለች፡፡ ነፍሱንም መላእክተ ብርሃን መጥተው ወደ ገነት አስገብተዋታል፡፡
ሁለተኛው ተአምር ደግሞ ከብሮ ከኖረ በኋላ ለድህነት በተጋለጠ አንድ ምእመን ላይ የተደረገ ነው፤ ከክርስቲያን ወገን የኾነ ሀብት አግኝቶ ያጣ አንድ ሰው ነበር፡፡ ከዕለታት አንድ ቀን “ከብሬ በኖርኹበት አገር ተዋርጄ አልኖርም” ብሎ ጓዙን ጠቅልሎ ከአገሩ ወጥቶ ሲሔድ ሰይጣን ያዘነ ሰው መስሎ ደንጊያውን በምትሐት ወርቅ አስመስሎ “ሥላሴን፣ ጻድቃንን፣ ሰማዕታትንን፣ መላእክትን ካድልኝና ይህን ወርቅ እሰጥሃለሁ” አለው፡፡ ዅሉንም ካደለትና ወርቁን ተቀብሎ ዞር ሲል “ምእመናን የሚመኩባት ድንግል ማርያም “የአምላክ እናት አይደለችም' ብለህ ካድልኝ” አለው፡፡ ሰወየውም “እርሷንስ አልክድም” ስላው በደንጊያ ቀጥቅጦ ገደለው፡፡ መላእክተ ጽልመት የሟቹን ነፍስ ሊወስዱ ሲሉ መላእክተ ብርሃንም አብረው ቀረቡ፡፡ እመቤታችንም ጌታችንን "ልጄ ይህችን ነፍስ ማርልኝ?” አለችው፡፡ እርሱም “ከልብኑ ይትመሐር እምየ፤ እናቴ፣ ውሻ ይማራልን?" አላት፡፡ እመቤታችንም፡- "‹ስምሽን የጠራውን፣ መታሰቢያሽን ያደረገውን እምርልሻለሁ› ያልኸው ቃል ይታበላልን?" አለችው፡፡ በዚህ ጊዜ "ምሬልሻለሁ" አላት፡፡
እግዚአብሔር አምላካችን "ከመረጥኳቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ" ባለው መሠረት ከቅዱሳን ጋር ያደረጋቸው ቃል ኪዳኖች ብዙዎች ናቸው፡፡ ከእነዚህም መካከል ከላይ በተአምራቱ እንደተመለከትነው አንዱ ለእመቤታችን የሰጠው የአማላጅነት ኪዳን ነው፡፡ ማማለድ ማለት ስለሌላው መጸለይ፣ መለመን፣ የደረሰውን ችግር እንዲወገድ ማድረግ፣ ማስማር (ይቅርታ ማሰጠት) ማለት ነው፡፡ በዚሁ መሠረት ከእግዚአብሔር በታች ከቅዱሳን ዅሉ በላይ ከፍ ከፍ ያለችና የከበረች እመቤታችን ቅድስት ድንግል ማርያም ከእግዚአብሔር በተሰጣት የማማለድ ሥልጣን "ሰአሊ ለነ ቅድስት፤ ቅድስት ሆይ ለምኚልን" እያሉ ለሚለምኗት ዅሉ ከእግዚአብሔር እያማለደችና እየለመነች ምሕረትን እንደምታሰጥ ቀናውንና የተመሰገነውን ሃይማኖት የምንከተል ምእመናን ዅሉ እናምናለን፡፡ ምክንያቱም ቅድስት ድንግል ማርያም የእግዚአብሔር እናትና አገልጋይ እንደመኾኗ ከዅሉም ቅዱሳን በበለጠ ለእግዚአብሔር ቅርብ ናትና፡፡ በእግዚአብሔር ዘንድም ኾነ በሰው ዘንድ ባለሟልነትን ማግኘት ወይም ቅርብ መኾን ደግሞ አንድን ጉዳይ በቀላሉ ለማስፈጸም ይጠቅማል፡፡ ለምሳሌ፡-
መልአኩ ቅዱስ ገብርአል በእግዚአብሔር ፊት የሚቆም ባለሟል በመኾኑ የድኅነትን ምሥጢር አብሣሪ ኾኗል /ሉቃ. ፩፥፲፱-፳፮/፡፡
አስቴር የንጉሡ አርጤክስስ ሚስት በመኾኗ በወገኖቿ አይሁድ የታወጀውን የሞት አዋጅ አስለውጣለች /መጽሐፈ አስቴር ፫፥፲/፡፡
ነቢዩ ሙሴ በእግዚአብሔር ፊት ባለሟል በመኾኑ "ይህንንኀጢአታቸውን ይቅር በላቸው፤ ያለዚያ ግን እኔን ከጻፍከው መጽሐፍህ እባክህ ደምስሰኝ?" በማለት ለእስራኤላውያን ምሕረትን አሰጥቷል /ዘፀ.፴፪፥፲፬/፡፡
ስለዚህ የቅድስት ድንግል ማርያም አማላጅነትም እንደ ፀሐይ የበራ ሐቅ ነው፡፡ ይህንን እውነት ቅዱስ ያሬድ ሲመሰክር፡- "ወታስተሠርዪ ኀጢአተ ሕዝብኪ ተበውሀ ለኪ እምአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ ወከመ ትኩኒ ተንከተመ ለውሉደ ሰብእ ለሕይወት ዘለዓለም፤ ለሕዝብሽ፣ ለወገኖችሽ የኃጢአት ይቅርታን ታሰጪ ዘንድ፤ ዘለዓለማዊ ሕይወትንም ለሚወርሱ ዅሉ መሸጋገሪያ ድልድይ ትኾኚ ዘንድ ከአብ ከወልድ ከመንፈስ ቅዱስ ዘንድ ሥልጣን አግኝተሻል" በማለት አመስግኗታል /አንቀጸ ብርሃን/፡፡ አባ ጽጌ ድንግልም በማኅሌተ ጽጌ ድርሰታቸው፡- "ሶበሰ ኪዳንኪ ምክንያተ ድኂን ኢሀሎ ፈለገ እሳት ወደይን እም አሰጠመ ኩሎ፤ የድኅነት ምክንያት ቃል ኪዳንሽ ባይኖር ኖሮ የጥፋት እሳት፣ መርገም (ኀጢአት) ባጠፋን ነበር" ብለዋል፡፡ አባ ሕርያቆስም በቅዳሴው፡– “ጥፋትን ያይደለ ይቅርታን አሳስቢ፡፡ መዓትን ያይደለ ምሕረትን አሳስቢ፡፡ ለጻድቃን ያይደለ ለኀጥአን አሳስቢ፡፡ ለንጹሐን ያይደለ ለተዳደፉት አሶስቢ፤” ሲሉ ይማጸኗታል /ቅዳሴ ማርያም ቍ.፻፷፭-፻፸፩/፡፡
ስለዚህም ዘወትር በሥርዓተ ቅደሴአችን፡- “ድኅነትን የምንለምንሽ ክብርን የተመላሽ ቅድስት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ዅል ጊዜ ድንግል የምትኾኚ አምላክን የወለድነሽ የክርስቶስ እናት ሆይ ኀጢአታችንን ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ልጅሽ ወደ ወዳጅሽ ወደ ላይ ጸሎታችንን አሰርጊልን፡፡ በእውነት የጽድቅ ብርሃን የሚሆን አምላካችንን ክርስቶስን የወለድሽልን ንጽሕት ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ ንጽሕት ድንግል ሆይ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግ ዘንድ፤ ኀጢአታችንንም ያስተሠርይልን ዘንድ ወደ ጌታችን ለምኚልን፡፡ በእውነት ለሰው ወገን አማላጅ የምትሆኝ አምላክን የወለድሽ ንጽሕት ቅድስት ድንግል ማርያም ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ የኀጢአታችንን ሥርየት ይሰጠን ዘንድ በልጅሽ በክርስቶስ ፊት ለምኝልን፡፡ በእውነት ንግሥት የምትኾኚ ንጽሕት ድንግል ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ የባሕርያችን መመኪያ ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ አምላካችን አማኑኤልን የወለድሽልን ሆይ ደስ ይበልሽ፡፡ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ፊት እውነተኛ አስታራቂ ሆነሽ ታስቢን ዘንድ እንለምንሻለን፡፡ ለነፍሳችን ይቅርታን ያደርግልን ዘንድ ኀጢአታችንንም ያስተሰርይልን ዘንድ፤" በማለት እመቤታችንን እንማጸናታለን፡፡
በአጠቃላይ "ኪዳነ ተካየድኩ ምስለ ኅሩያንየ፤ ከመረጥኋቸው ጋር ቃል ኪዳን አደረግሁ፤" በማለት በነቢዩ ቅዱስ ዳዊት አድሮ ራሱ እግዚአብሔር ከመረጣቸው አበው ነቢያት፣ ጻድቃን፣ ቅዱሳንና ሰማዕታት ጋር ቃል ኪዳን እንደ ገባ፣ እንደሚገባ ተናግሯል /መዝ.፹፰፥፫/፡፡ ሐዋርያው ቅዱስ ጳውሎስም "እንግዲህ እርሱ ራሱ ካጸደቀ እግዚአብሔር የመረጣቸውን ሰዎች የሚቃወማቸው ማን ነው?" በማለት እግዚአብሔር ሰዎችን እንደሚጠራ፣ እንደሚያከብር፣ እንደሚቀድስና ቃል ኪዳን እንደሚሰጥ ነግሮናል /ሮሜ.፰፥፴፫/፡፡ ቅዱስ ዳዊት "ነኪር ነገሩ በእንቲአኪ ሀገረ እግዚአብሔር፤ የእግዚአብሔር ከተማ ሆይ ስለ አንቺ የተነገረው ነገር ድንቅ ነው፤" /መዝ.፹፮፥፫/ በማለት እንደተናገረው እግዚአብሔር አምላካችን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የገባው ቃል ኪዳን ከቅዱሳን ቃል ኪዳን ዅሉ ልዩ ነው፡፡ ይህም እንደምን ነው ቢሉ፡-
ለአምላክ እናትነት የተመረጠች ልዩ እናት በመኾኗ፤
አምላክ ከሥጋዋ ሥጋ፣ ከነፍሷ ነፍስ ነሥቶ ከእርሷ በመወለዱ፤
ከመለለዷ በፊት፣ በወለደች ጊዜ፣ ከወለደች በኋላ ምን ጊዜም ድንግል በመኾኗ፤
በሁለቱም ወገን (በአሳብም በገቢርም) ድንግል በመኾኗ፤
አማላጅነቷ የወዳጅነት ሳይኾን የእናትነት በመኾኑ፤
ዓለም ይድን ዘንድ የድኅነት ምክንያት አድርጎ አምላክ ስለመረጣት ነው፡፡
ስለዚህ ብዙ ከንቱ አሳቦችን ትተን፣ እንደበላዔ ሰብእ በቃል ኪዳኗ ተጠቅመን፣ ንስሐ ገብተን፣ ቅዱስ ሥጋውን ክቡር ደሙን ተቀብለን፣ የስሙ ቀዳሽ፣ የመንግሥቱ ወራሽ ለመኾን ያብቃን፡፡ የእግዚአብሔር ቸርነት፣ የእመቤታችን አማላጅነት፣ የቅዱሳን ተራዳዒነት አይለየን፡፡
https://youtu.be/alaGdCJDanI
❖ The Covenant of Mercy Kidane Mehret (ኪዳነ ምሕረት)❖
❖ Yekatit 16 / February 23 – The Covenant of Mercy – Kidane Mehret (ኪዳነ ምሕረት) ❖
Kidane Mehret is a Ge'ez phrase meaning the Covenant of Mercy, which is celebrated on 16 Yekatit / February 23. According to the Ethiopian Orthodox Tewahedo Church tradition and order, the Feast of Kidane Mehret is one of the 33 Feasts of Holy Virgin Saint Mariam. On this day Our Holy Mother received the Covenant of Mercy from her Son Eyesus Kristos as was written in the Holy Book of Te'amire Mariam.
❖❖
“ I have made a covenant with my chosen”
The Covenant of Mercy From the Book of the Miracles Saint Mariam
(Te’amire Mariam)
One day our Lord and Savior Eyesus Kristos said unto Holy Virgin Mariam, "What sorrow can be greater than that which came upon thee for My sake?" And our Lady Mariam said unto Him, "O my Lord and God, there were Five Sorrows that came upon me for Thy sake, and they overcame me mightily.
1. The First of them was that which came upon me when Simeon prophesied concerning Thee in the Sanctuary, saying that the Jews would slay Thee.
2. The Second was the sorrow I endured when I lost Thee in the Sanctuary, and I was seeking for Thee for three days.
3. The Third was the sorrow I endured when I remembered how they had bound Thee hand and foot, and how Pilate's men scourged Thy back.
4. The Fourth was the sorrow I endured when they crucified Thee between two thieves on the day of the Eve of the Sabbath, and Thou wast naked, and they drove five nails through Thy flesh.
5. The Fifth sorrow I endured when I remembered how Joseph and Nicodemus took Thee down from the Cross, and swathed Thee in fine linen, and laid Thee in the tomb."
And our Lord said unto her who had given Him birth, "Thus saith our Father Who is in heaven: Whosoever shall keep in remembrance the sorrows and sufferings which have come upon thee for My sake, and the salutation of Gabriel, I will remit to him his sins. And whosoever shall give an offering for thy name's sake I will remit to him his sins, and I will make him to inherit the kingdom of heaven. And I will come unto him with thee, O thou who didst give Me birth, and I will appear to him three days before his death." This was the Covenant, which Christ made with His Holy Mother, and She told it unto Dexius, who wrote it down, together with Her Miracles, so that all believers might read it.
May Kidane Mehret's prayer and blessing be with us forever and ever. Amen!
_______
_______
Comments