top of page

በአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ላይ የዘመቱት የርኩሳን ዘር-አጥፊ ነፍሰ ገዳዮች ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ኹለተኛው ሞት ነው


https://youtu.be/l4TtxHuCNmA

✤<ራዕይ ዮሐንስ ምዕራፍ ፳፩፥፰>✤“ዳሩ ግን የሚፈሩና የማያምኑ የርኩሳንም የነፍሰ ገዳዮችም የሴሰኛዎችም የአስማተኛዎችም ጣዖትንም የሚያመልኩ የሐሰተኛዎችም ዅሉ ዕድላቸው በዲንና በእሳት በሚቃጠል ባሕር ነው፤ ይኸውም ኹለተኛው ሞት ነው።”

❖<የዮሐንስ ራእይ ምዕራፍ ፳፩>❖ ፩ ፤ዐዲስ፡ሰማይንና፡ዐዲስ፡ምድርንም፡አየኹ፥ፊተኛው፡ሰማይና፡ፊተኛዪቱ፡ምድር፡ዐልፈዋልና፥ባሕርም፡ወደ፡ፊ ት፡የለም። ፪፤ቅድስቲቱም፡ከተማ፡ዐዲሲቱ፡ኢየሩሳሌም፥ለባሏ፡እንደተሸለመች፡ሙሽራ፡ተዘጋጅታ፥ከሰማይ፡ከእግዚአብሔር፡ ዘንድ፡ስትወርድ፡አየኹ። ፫፤ታላቅም፡ድምፅ፡ከሰማይ፦እንሆ፥የእግዚአብሔር፡ድንኳን፡በሰዎች፡መካከል፡ነው፥ከነርሱም፡ጋራ፡ያድራል፥እ ነርሱም፡ሕዝቡ፡ይኾናሉ፡እግዚአብሔርም፡ርሱ፡ራሱ፡ከነርሱ፡ጋራ፡ኾኖ፡አምላካቸው፡ይኾናል፤ ፬፤እንባዎችንም፡ዅሉ፡ከዐይኖቻቸው፡ያብሳል፥ሞትም፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይኾንም፥ሐዘንም፡ቢኾን፡ወይም፡ጩኸ ት፡ወይም፡ሥቃይ፡ከእንግዲህ፡ወዲህ፡አይኾንም፥የቀደመው፡ሥርዐት፡ዐልፏልና፥ብሎ፡ሲናገር፡ሰማኹ። ፭፤በዙፋንም፡የተቀመጠው፦እንሆ፥ዅሉን፡ዐዲስ፡አደርጋለኹ፡አለ።ለኔም፦እነዚህ፡ቃሎች፡የታመኑና፡እውነተኛዎ ች፡ናቸውና፥ጻፍ፡አለኝ። ፮፤አለኝም፦ተፈጽሟል።አልፋና፡ዖሜጋ፥መዠመሪያውና፡መጨረሻው፡እኔ፡ነኝ።ለተጠማ፡ከሕይወት፡ውሃ፡ምንጭ፡እን ዲያው፡እኔ፡እሰጣለኹ። ፯፤ድል፡የሚነሣ፡ይህን፡ይወርሳል፡አምላክም፡እኾነዋለኹ፡ርሱም፡ልጅ፡ይኾነኛል። ፰፤ዳሩ፡ግን፡የሚፈሩና፡የማያምኑ፡የርኩሳንም፡የነፍሰ፡ገዳዮችም፡የሴሰኛዎችም፡የአስማተኛዎችም፡ጣዖትንም፡ የሚያመልኩ፡የሐሰተኛዎችም፡ዅሉ፡ዕድላቸው፡በዲንና፡በእሳት፡በሚቃጠል፡ባሕር፡ነው፤ይኸውም፡ኹለተኛው፡ሞት ፡ነው። ፱፤ሰባቱም፡ዃለኛዎች፡መቅሠፍቶች፡የሞሉባቸውን፡ሰባቱን፡ጽዋዎች፡ከያዙት፡ከሰባቱ፡መላእክት፡አንዱ፡መጥቶ፦ ወደዚህ፡ና፥የበጉንም፡ሚስት፡ሙሽራዪቱን፡አሳይኻለኹ፡ብሎ፡ተናገረኝ። ፲፥፲፩፤በመንፈስም፡ወደ፡ታላቅና፡ወደ፡ረዥም፡ተራራ፡ወሰደኝ፥የእግዚአብሔርም፡ክብር፡ያለባትን፡ቅድስቲቱን፡ ከተማ፡ኢየሩሳሌምን፡ከሰማይ፡ከእግዚአብሔር፡ዘንድ፡ስትወርድ፡አሳየኝ፤ብርሃኗም፡እጅግ፡እንደ፡ከበረ፡ድን ጋይ፡እንደ፡ኢያሰጲድ፡ድንጋይ፡ኾኖ፡እንደ፡ብርሌ፡የጠራ፡ነበረ፤ ፲፪፤ታላቅና፡ረዥም፡ቅጥር፡ነበራት፥ዐሥራ፡ኹለትም፡ደጆች፡ነበሯት፡በደጆቹም፡ዐሥራ፡ኹለት፡መላእክት፡ቆሙ፥ የዐሥራ፡ኹለቱም፡የእስራኤል፡ልጆች፡ነገዶች፡ስሞች፡ተጽፈውባቸው፡ነበር። ፲፫፤በምሥራቅ፡ሦስት፡ደጆች፥በሰሜንም፡ሦስት፡ደጆች፥በደቡብም፡ሦስት፡ደጆች፥በምዕራብም፡ሦስት፡ደጆች፡ነበሩ። ፲፬፤ለከተማዪቱም፡ቅጥር፡ዐሥራ፡ኹለት፡መሠረቶች፡ነበሯት፥በእነርሱም፡ውስጥ፡የዐሥራ፡ኹለቱ፡የበጉ፡ሐዋርያ ት፡ስሞች፡ተጽፈው፡ነበር። ፲፭፤የተናገረኝም፡ከተማዪቱንና፡ደጆቿን፡ቅጥሯንም፡ይለካ፡ዘንድ፡የወርቅ፡ዘንግ፡ነበረው። ፲፮፤ከተማዪቱም፡አራት፡ማእዘን፡ነበራት፥ርዝመቷም፡እንደ፡ስፋቷ፡ልክ፡ነበረ።ከተማዪቱንም፡በዘንግ፡ለካት፡ ዐሥራ፡ኹለትም፡ሺሕ፡ምዕራፍ፡ኾነች፤ርዝመቷና፡ስፋቷ፡ከፍታዋም፡ትክክል፡ነው። ፲፯፤ቅጥሯንም፡ለካ፥መቶ፡አርባ፡አራት፡ክንድ፡በሰው፡ልክ፥ርሱም፡በመልአክ፡ልክ። ፲፰፤ቅጥሯም፡ከኢያሰጲድ፡የተሠራ፡ነበረ፥ከተማዪቱም፡ጥሩ፡ብርጭቆ፡የሚመስል፡ጥሩ፡ወርቅ፡ነበረች። ፲፱፤የከተማዪቱም፡ቅጥር፡መሠረት፡በከበረ፡ድንጋይ፡ዅሉ፡ተጌጦ፡ነበር፤ፊተኛው፡መሠረት፡ኢያሰጲድ፥ኹለተኛው ፡ሰንፔር፥ሦስተኛው፡ኬልቄዶን፥አራተኛው፡መረግድ፥ ፳፤ዐምስተኛው፡ሰርዶንክስ፥ስድስተኛው፡ሰርድዮን፥ሰባተኛው፡ክርስቲሎቤ፥ስምንተኛው፡ቢረሌ፥ዘጠነኛው፡ወራ ውሬ፥ዐሥረኛው፡ክርስጵራስስ፥ዐሥራ፡አንደኛው፡ያክንት፥ዐሥራ፡ኹለተኛው፡አሜቴስጢኖስ፡ነበረ። ፳፩፤ዐሥራ፡ኹለቱም፡ደጆች፡ዐሥራ፡ኹለት፡ዕንቍዎች፡ነበሩ፤እያንዳንዱ፡ደጅ፡ካንድ፡ዕንቍ፡የተሠራ፡ነበረ።የ ከተማዪቱም፡አደባባይ፡ጥሩ፡ብርጭቆ፡የሚመስል፡ጥሩ፡ወርቅ፡ነበረ። ፳፪፤ዅሉንም፡የሚገዛ፡ጌታ፡አምላክና፡በጉ፡መቅደሷ፡ናቸውና፥መቅደስ፡በርሷ፡ዘንድ፡አላየኹም። ፳፫፤ለከተማዪቱም፡የእግዚአብሔር፡ክብር፡ስለሚያበራላት፡መብራቷም፡በጉ፡ስለ፡ኾነ፥ፀሓይ፡ወይም፡ጨረቃ፡እን ዲያበሩላት፡አያስፈልጓትም፡ነበር። ፳፬፤አሕዛብም፡በብርሃኗ፡ይመላለሳሉ፥የምድርም፡ነገሥታት፡ክብራቸውን፡ወደ፡ርሷ፡ያመጣሉ፤ ፳፭፤በዚያም፡ሌሊት፡ስለሌለ፡ደጆቿ፡በቀን፡ከቶ፡አይዘጉም፥ ፳፮፤የአሕዛብንም፡ግርማና፡ክብር፡ወደ፡ርሷ፡ያመጣሉ። ፳፯፤ለበጉም፡በኾነው፡በሕይወት፡መጽሐፍ፡ከተጻፉት፡በቀር፥ጸያፍ፡ነገር፡ዅሉ፡ርኵሰትና፡ውሸትም፡የሚያደርግ ፡ወደ፡ርሷ፡ከቶ፡አይገባም።

_______

_______

 
 
 

Comments


bottom of page