SecState Marco Rubio Appears on Television With The Ashes CROSS on His Forehead
- Abraham Enoch
- Mar 7
- 3 min read
https://youtu.be/y8F4AxJqevA
✞ የአሜሪካ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ አመድ መስቀል ግንባሩ ላይ ሆኖ በቴሌቪዥን ታየ
የቃለ ምልልሱ አላማ እንደ ዩክሬን ጦርነት እና የጋዛ ግጭት ባሉ የአለም አቀፍ ፖለቲካ ጉዳዮች ላይ ለመወያየት ቢሆንም የህዝቡ ትኩረት በፍጥነት ወደ ሩቢዮ ሀይማኖታዊ ተምሳሌትነት ተቀየረ።
የዩናይትድ ስቴትስ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ማርኮ ሩቢዮ ዛሬ ረቡዕ በጠዋቱ የፎክስ ኒውስ ትርኢት ላይ በካቶሊኮች 'የአመድ እሮብ' ዕለት መስቀል ግንባሩ ላይ መታየቱን ተከትሎ ከፍተኛ ክርክር አስነስቷል።
ካቶሊኮች ዐብይ ጾም ከመጀመሩ በፊት ባለው ረቡዕ ቀን በዐመድ የመቀባት ሥርዓት አላቸው
በካቶሊክ ቤተክርስቲያን ሥርዐተ አምልኮ ደንብ መሰረት የዐብይ ጾም የሚጀመረው ቄሳውስት የምዕመናንን ግንባር በአመድ የመቀባት ሥርዐት ካከናወኑ በኋላ ነው። በጎርጎሮሳዊያኑ የቀን አቆጣጠር የላቲን ሥርዐተ አምልኮ በምትከተለው የካቶሊክ ቤተክርስቲያን የሥርዐተ አምልኮ ደንብ መሰረት የዐብይ ጾም የተጀመረው ያለፈው ረቡዕ እለት የካቲት 05/2025 ዓ.ም ግንባርን በዐመድ የመቀባት ስርዓት ከተደረገ በኋላ ሲሆን ይህም ለመጪዎቹ አርባ ቀናት ምጽዋዕት በመስጠት፣ በጸሎት፣ በጾም የሚፈጸመው ጾም እግዚኣብሔርን የሚያስደስት ጾም ይሆን ዘንድ፣ ለጿሚው ሰው ደግሞ መንፈሳዊ ጸጋ የሚያስገኝለት ጾም ይሆን ዘንድ፣ እንዲሁም የፋሲካን በዓል ዋና ትርጉሙን በጠበቀ መልኩ ለማክበር ይቻል ዘንድ መንፈሳዊ ዝግጅት የሚደረግበት ወቅት ነው።
ዐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ሁለት ዓይነት ትርጉሞች አሉት። በቅድሚያ የሰው ልጅ በጌታ ፊት ደካማ እና ያልተገባ መሆኑን የሚያመለክት ሲሆን በዚህ ረገድ አብርሃም “እኔ ከንቱ ትቢያና ዐመድ ሆኜ ሳለሁ ከጌታ ጋር ለመነጋገር እንዴት እደፍራለሁ” (ኦሪት ዘፍጥረት. ፲፰፥፳፯) በማለት የሰው ልጆች ለእግዚኣብሔር ያልተገቡ ደካሞች መሆናቸውን ይገልጻል። ኢዮብ አበበኩሉ የሰው ልጅ ውስን መሆኑን ለመግለጽ በማሰብ “እርሱ በጭቃ ውስጥ ጣለኝ፥ አፈርና አመድም መሰልሁ” (ኢዮብ ፴፥፲፱) በማለት ስብዕናችን ውስን መሆኑ ይገልጻል። በመጽሐፈ ጥበብ ውስጥ ደግሞ “እኛ በከንቱ ተፈጥረናልና፣ ከእዚያን በኋላ እንዳልተፈጠርን እንሆናለን፣ በአፍንጫችን ያለ ትንፋሻችን እንደ ጢስ ነውና። በልቡናችንም እንቅስቃሴ የብል ጭልጭታ ቃል አለና። ከሞት በኃላ ሥጋችን ትቢያ ይሆናል፣ መነፈሳችንም እንደ ጉም ተን ይበተናል” (ጥበብ ፪፥፪፡፫)። የሰው ልጅ ከአፈር መሰራቱን ወደ አፈር እንደ ሚመለስ ይገልጻል። ሲራክ በትንቢቱ “እንግዲህ ትቢያ እና ዐመድ የሚሆን በሕይወትም ሳለ ሰውነት የሚተላ ሰው ስለምን ይታበያል?” (ሲራክ ፲፡፱) በማለት የትዕቢት መጀመሪያ ሰውን ከእዚኣብሔር እንደ ሚለይ ልቦናውንም ከእግዚኣብሔር እንደ ሚያርቅ፣ ትዕቢት የኃጢአት መጀመሪያ መሆኑን እና በሰው ልጅ ላይ እርኩሰትን የማብዛት አቅም እንዳለው በመግለጽ፣ በተቃራኒው ደግሞ እግዚኣብሔር ትዕቢተኞችን ሰለማይወድ እና ስለሚያጠፋቸው ጭምር ከትዕቢት ርቀን ወደ እግዚአብሔር እንድመለስ ጥሪ ያቀርባል።
ዐመድ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ ያለው ሁለተኛ ትርጉም ደግሞ የሰው ልጅ በሰራው ኃጢአት መጸጸቱን የሚያሳይ ምልክት ነው። ለዚህም በዋቢነት የሚቀርበው ምሳሌ የነቢዩ ዮኖስ ታሪክ ሲሆን ነቢዩ ዮናስ እግዚኣብሔር በላከው መሰረት በወቅቱ በሰሩት ከፍተኛ ኃጢአት ምክንያት ከእግዚኣብሔር ርቀው የነበሩ የነኔዌ ሰዎችን በሰሩት ኃጢአት ምክንያት ተጸጽተው ማቅ ለብሰው በዐድ ላይ ቁጭ እንዲሉ እግዚኣብሔር በዛዘው መሰረት ይህንን የትንቢት ቃል እንደ ነገራቸው የሚታወስ ሲሆን እነርሱም ከነኔዌ ንጉሥ ጭምር ሁሉም በሰሩት ክፉ ነገር እና ኃጢአት ምክንያት ተጸጽተው ማቅ ለብሰው በዐመድ ላይ በመቀመጣቸው የተነሳ እግዚኣብሔር ምሕረትን እንዳደረገላቸው ይታወቃል። በእነዚህ ምክንያቶች የተነሳ ነው እንግዲህ ዐብይ ጾምን ከመጀመራቸውን በፊት ባለው ረቡዕ ቀን የሰው ልጆች ደካሞች፣ ያለእግዚኣብሔር ድጋፍ ከንቱ መሆናችንን በማስተወስ እና በመቀጠልም በኃጢአታቸው መጸጸታቸውን ለመግለጽ በማሰብ ዐብይ ጾም ከመጀመራቸው በፊት በዐመድ ግንባራቸውን የሚቀቡት በዚሁ ምክንያት ነው።
አመድ መስቀል የተመልካቾችን ግንባር የሚያመለክተው ሟችነትን እና ለኃጢአታቸው ንስሐ መግባትን ለመወከል ነው። አመዱ በማለዳ ቅዳሴ ጊዜ በካህኑ ይተገበራል፣ ብዙውን ጊዜ ከትንሽ በረከት ጋር "አፈር እንደ ሆንህ አስብ ወደ አፈርም ትመለሳለህ።" ብዙዎች ምዕመናን ቀኑን ሙሉ ግንባራቸው ላይ ` ተቀብተው መስቀሉን ለማቆየት ይመርጣሉ።
✞ Although the aim of the interview was to discuss topics of international politics, such as the war in Ukraine and the conflict in Gaza, public attention quickly shifted to Rubio's religious symbolism.
The United States Secretary of State, Marco Rubio, sparked intense debate following his appearance this Wednesday on the morning show of Fox News with the Ash Wednesday cross marked on his forehead.
Catholics mark Ash Wednesday, the beginning of Lent. The cross, made of ashes, symbolizes repentance and is traditionally placed by a priest.
The ash Cross marking observers' foreheads is meant to represent mortality and penance for their sins. It is applied by a priest during a morning mass, often along with a small blessing: "Remember that you are dust and to dust you shall return." Many choose to keep it on all day.
_______
_______
Comments