top of page

የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል


https://youtu.be/X-xyNDZ5630

❖❖❖ ስብሐት ለአብ ፡ ስብሐት ለወልድ ፡ ስብሐት ለመንፈስ ቅዱስ፤ አሜን! () ❖❖❖

ሰይፈ ሥላሴ በተለይ በረቂቅ የሚዋጉንን አጋንንት በረቂቅ የጸሎቱ ሰይፍ ስለሚቆርጥልን አጋንንት ወደ እኛ እንዳይቀርቡ ያደርግልናል፡፡ ሰይፈ ሥላሴን ዘወትር የሚጸልየው ሰው አጋዕዝተ ዓለም ሥላሴ በረድኤት፣በመለኮታዊ ጥበቃነት አይለዩትም፡፡ ከቤቱ የሥላሴ በረከት አይታጣም፡፡ ጠላት አይበረታበትም፡፡ አጥር አፍርሶ፣ድንበር ጥሶ የሚመጣን ግልጽም ይሁን ስውር ጠላትን ያርቃል፣ይሰውራል፡፡

በተለይ ዓይነ ጥላ፣ መተት ድግም፣ዛር ወዘተ ያለበት ሰው ሰይፈ ሥላሴን ያለመሰልቸት፣ያለ መታከት አዘውትሮ ቢጸልየው በላዩ ላያ ያደረበት መንፈስ እድሜው እያጠረ፣እንደ ጢስ እየበነነ እንደ ጉም እየተበተነ ይሄዳል፡፡ አጋንንትን ከሚያዳክሙት፣አጋንንታዊ ኃይሉን ከሚነሱት ጸሎቶች ውስጥ አንዱ ሰይፈ ሥላሴ ነው፡፡ የሰይፈ ሥላሴ ጸሎት በሥጋም በነፍስም፣ አጋንንት ውጊያም ጥቅም ኃይለኛ እና ድንቅ በመሆኑ ጸሎቱን ማዘውተር ይገባናል፡፡

ሰይፈ ሥላሴን በመጸለይ ሁለት ዋና ጥቅም እናገኛለን፡፡ አንደኛው አጋዕዝተ ሥላሴን እናመሰግናለን፡፡ ሁለተኛ በጸሎት ኃይል እራሳችን እንጠበቅበታለን፡፡ ስለዚህ ሰይፈ ሥላሴን አዘውትረን መጸለይ አንዱ ውዴታችን ሳይሆን ግዴታችን ሊሆን ይገባል፡፡

ቅዱስ ዮሐንስ በራዕዩ ”ዲያቢሎስ ጥቂት ዘመን እንዳለው አውቆ በታላቅ ቁጣ ወደ እናንተ ወርዷልና” ብሎ ስለነገረን ወደ ሕይወታችን በቅናት ቁጣ እየመጣ የሚያመሰቃቅለንን፣ ግራ የሚያጋባንን፣ የሚያባክነንን፣ የእኛ የሆነውን የሚነጥቀንን ዲያቢሎስ በሰይፈ ሥላሴ ጸሎት ልናርቀው እና ልንርቀው ይገባል፡፡ <ራዕ. ፲፪÷፲፪>ራዕ. ፲፪÷፲፪>

ሰሜን ኢትዮጵያውያን በተለይ የትግራይ ኢትዮጵያውያን ዲያብሎስ የእናንተ የሆነውን ኢትዮጵያዊነትን፣ ተዋሕዶ ክርስትናን፣ የጽዮንን ሰንደቅን፣ ግዕዝ ቋንቋን ብሎም ድንግል ነፍሳችሁን ሊነጥቃቸው ዳርዳር በማለት ላይ ነውና ዋ! በጣም ተጠንቀቁ! እንጠንቀቅ!

❖❖❖ የሥላሴ ረድኤት በረከታቸው አይለየን፤ አሜን! () ❖❖❖

___________________________

Comentários


bottom of page