ወደ ሕፃናቶቻችን መጡ
- Abraham Enoch
- Jul 7, 2013
- 15 min read
/ ቁሳቁሳዊ ድህነታችን ዋናውና ውዱን ኃብታችንን : መንፈሣዊ እኛነታችንን እየተፈታተነ ያቃውስብናል።
የሕብረተሰባችን ዋና ምሰሶዎች የሆኑት ሕፃናቶቻችንና ሴቶቻችን ለዚህ ዲያብሎሳዊ ጥቃት በቅድሚያ እየተጋለጡ እንደሆነ አሁን የምናየው ነው። ለመንፈሳዊ ሕይወታችን ጤንነት እናቶቻችን፣ እህቶቻችን፣ ሴት ልጆቻችን እና ሚስቶቻችን በጣም ከፍተኛ የሆነ ሚና ይጫወታሉ። በአገራችን ሕዝቦችን ዘንድ ጤናማ የሆነ የመንፈሳዊ ኑሮ እንዲጸባረቅ የሚያደርጉት የተቀደሰ ሥራቸው የማይነገርላቸው ሴቶቻችን ናቸው። ታዲያ ይህን የሚያውቀው ዲያብሎስ ሴቶቻችንና ሕጻናቶቻችንን ወስዶብን ለገዛ ልጆቹ ሊሰጥብን በየበረሃውና በየኮንቴነሩም ነፍሳቸውን እየመጠጠ ሊወስድባቸው ይሞክራል፣ እግረመንገዱንም ሕዝባችንን ለማዋረድ ፤ የአምላካችንንም ክብር ለመቀነስ ሲታገል ይታያል።
አንድ አጎቴ እንዳጫወቱኝ፤ ለንጉሥ ኃይለስላሴ ከዙፋን መውረድ ምክኒያት የሆነውን አስከፊ የኢትዮጵያ ረሃብ የፈጠሩት የዲያብሎስ ኃይሎች፤ የተራበውን ሕዝባችንን እንረዳለን በማለት ብዛት ያላቸውን ወታደሮቻቸውን ወደ ሰሜኑ የኢትዮጵያ ክፍል ልከው ነበር። እነዚህ ወታደሮች (የ 'ኔቶ' ሠራዊት መሆናቸው ነው) ከየትምህርት ቤቱ የሚወጡትን ሕፃናቶቻችንን ድንኳኖቻቸው እያስገቡ ሲያባልጉ ነበር።
በአሁኑም ጊዜ እነዚህ የዲያብሎስ አርበኞች አሳቢ፣ ረጂና ኢትዮጵያን ወዳጅ መስለው በህፃናቶቻችን ላይ ለህሊና የሚቀፉ እጅግ በጣም አደገኛ ድርጊቶችን በመፈጸም ላይ ይገኛሉ። ከነዚህ ውስጥ በተለይ ሰዶማውያን፣ አየራችንን፣ ምግባችንን እየበከሉ (ስንዴ ከአውስትራሊያ፣ ማዳበሪያ ከሳውዲ ዓረቢያ) ኪኒኑንና ክትባቱን እይቀመሙ ሕዝባችንን በመመረዝ ላይ ይገኛሉ። አባለዘሩን በ16ኛው ኤይድሱን ደግሞ በ20ኛው ክፍለዘመናት በሕዝባችን ዘንድ አሠራጭተው አደከሙት፤ አሁን በማገገሚያ ዘመናችን ደግሞ ሞራሉንና መንፈሣዊ ጤናውን በማናጋት ላይ ይገኛሉ።
ሰዶማዊነት በይበልጥ ተስፋፍቶ የሚታየው በአውሮፓ፡ አሜሪካ እና አረብ አገሮች ነው። ለምን? በእነዚህ አካባቢዎች የሚኖሩ ሕዝቦች ከእግዚአብሔር አምላክ የራቀውን መንገድ ስለመረጡ፣ ለስጋቸው ብቻ መኖሩን እና ከትክክለኛው የመንፈሣዊ ኑሮ ስለራቁ ነው። ለዚህ እምነት-ዓልባ ሥጋዊ ኑሮ ከፍተኛውን አስተዋጽኦ ያበረከተው የፕሮቴስታንቶች እምነት እንደሆነ የራሳቸው ባለሙያዎች አሁን በግልጽ ይናገራሉ። ከእግዚአብሔር አምላክ የራቀ ወደ ዲያብሎስ ሰፈር የመግባት እድሉ ከፍተኛ ነው። በዲያብሎስ ሰፈር የሚገኙት ደግሞ የተለያዩ ሆነው ቢታዩንም ዓላማቸው አንድ ነው፤ ይህም የእግዚአብሔርን ልጆች መዋጋት ነው።
ለሴቶች መብት እንዋጋለን፣ ለ "ጭቁን ፍልስጤማውያን" እንቆረቆራለን ከሚሉት ምዕራባውያን መካከል በብዛት ሰዶማውያን ይገኙበታል። ሙስሊም አረቦች በሰዶማዊያን ላይ የጥላቻ ዘመቻ አወጁ፡ እነርሱን ገደሉ፣ ሰቀሉ ይባላል፡ ነገር ግን እነዚህ ፌሚኒስቶች እና ሰዶማውያን በሙስሊሙ ዓለም ስለሚካሄደው የሴቶች በደል ወይም በክርስቲያኖች ላይ ስለሚካሄደው የጭፍጨፋ ዘመቻ አንዲትም ትንፍሽ አይሉም። ለምን? የሁሉም መንፈስ አንድ ዓይነት እና የዲያብሎስ መንፈስ ስለሆነ። ለዚህም ነው ምዕራባውያኑ 'ልዩ' የዓለማችን አስተዳዳሪዎች አክራሪ እስልምናን፣ ሰዶማዊነትን በይበልጥ እየተጠቀሙ ማሕበረሰባቱን በማድከም ላይ የሚገኙት፡ ለዚህም ነው ለአረቡ ዓለም እና ለሰሜን አፍሪቃ አገራት የምናየውን ያህል ከፍተኛ ትኩረት የሚሰጡት።
የተቀረው አፍሪቃ (ከሳሃራ በታች ብለውታል) ግን ድብቃዊ በሆነ መልክ በሽታውንም፣ ጦርነቱንም፣ ግብረ ሰዶማዊነቱንም ቀስበቀስ እንዲያስፋፋ ይቆሰቁሱታል። አፍሪቃውያን ባጠቃላይ ጸረ-ሰዶማዊ የሆነ ተፈጥሮ ስላላቸው፡ ሰዶማዊነት የነጮች በሽታ ብቻ እንዳልሆነ ለማሳየት ሆሊውድ የገቡትን ጥቁር አክተሮች እየበከሉ እና በጨረረ እየጠበሱ ወደ ሰዶማዊነት ለመቀየር እየሞከሩ ነው። በቅርቡ አንድ ጥቁር የኔቢኤ ባስኬትቦል ተጫዋች "ሰዶማዊ ነኝ!” ብሎ ቴሌቪዥን ላይ መቅረቡ አንዱ ማስረጃ ነው።
አደገኛዎቹ ሰዶማውያን፡ ከማርያም መቀነት የተወሰደውን የሰንድቅ ዓላማችንን ቀለማት ሰርቀዋል፡ በአሁኑ ጊዜም በተለይ በኢትዮጵያ ሕፃናት ላይ የዘንዶ ዓይናቸውን አነጣጥረዋል። ለምን? አንድም ሕፃናቶቻችን ብዙ መንፈሳዊ ኃብት የሚያንጸባርቅ ገጽታ ስላላቸው፤ በመንፈስ ሃብታም ስለሆኑ፡ እርሱን ለመንጠቅ፣ ሌላው ደግሞ ሰዶማውያን ቡናማ ቀለም ያላቸውን ሰዎች ስለሚመርጡ ርካሽ የስጋዊ ፍላጎታቸውን ለማሟላት ሰለሚመኙ ነው።
"ሰርከስ ኢትዮጵያ" በመባል የሚታወቀው የአገራችን የሕፃናት ሰርከስ ቡድን ቆርቆሪ የነበረውን ሰዶማዊ የካናዳ ሰው በአንድ ወቅት፡ "ለምን ወደ ኢትዮጵያ ልጆች አተኮርክ?” ብዬ ከመሞቱ በፊት ጠይቄው ነበር። የሰጠኝም መልስ፡ "በጣም ተጎድተው በማዬቴ ለመርዳት ነው" በማለት መልሶልኝ ነበር። አዎ! በጎ ሃሳብ ያላቸው፣ የተባረኩና የመላእክ ያህል ሩህሩህ ባሕርይ ያላቸው ፈረንጆች አሉ። ነገር ግን እነዚህ ብሩክ ሰዎች ወደ ኢትዮጵያ የመሄድ እድላቸው እጅግ በጣም የመነመነ ነው። ማለትም፣ ከኢትዮጵያ ጋር ግኑኝነት ያላቸው ፈረንጆች ለልዩ ተልዕኮ የራሳቸውን ጥቅም የሚያስቀድሙት፡ አልፎአልፎም የኛን ውድቀት የሚመኙት ናቸው። ቀን ላይ ሁኔታቸው የተለመደ ሆነው የሚታዩን ሰዎች ማታ ማታ ባልጠበቅነው መልክ ጋኔናዊ ስነሥርዓቶችን የሚካሂዱ፡ ምናልባትም እንደ ቫምፓየር ደም መጣጮች ሊሆኑ ይችላሉ። ይህን ሃቅ ወደድንም ጠላንም መቀበል ይኖርብናል።
ሌላው ምሳሌ፤ የጥንታውያን ሰዎች አጥንት እንፈልጋልን ብለው ወደ ኢትዮጵያ የመጡት አሜሪካዊ የአርኪዎሎጂ ሊቅ፣ ዶናልድስ ዮሐንሰን፡ ታዋቂዋን "ሉሲ" ሉሲ የሚለውን ስም የሰጧት፡ አጽሞቿን ባገኙበት ወቅት የእንግሊዛዊውን የሙዚቃ ቡድን፣ የ 'ቢትልስን" ዘፈን "Lucy in the Sky With Diamonds” እያዳመጡ ስለነበር ገልጠውልናል። ግን ይህ እውነት ነውን? ሉሲ የሚለው ቃል "Luce” ከሚለው የላቲን ቃል የመነጨ ሲሆን፡ ትርጉሙም "ብርሃን" ማለት ነው። Lucifer ብርሃኑ ክርስቶስ ሳይሆን እኔ ነኝ ይላል። እግዚአብሔር ግን እንዲህ ይለዋል፡
“አንተ የንጋት ልጅ አጥቢያ ኮከብ ሆይ፥ እንዴት ከሰማይ ወደቅህ! አሕዛብንም ያዋረድህ አንተ ሆይ፥ እንዴት እስከ ምድር ድረስ ተቈረጥህ! አንተን በልብህ። ወደ ሰምይ ዐርጋለሁ፥ ዙፋኔንም ከእግዚአብሔር ከዋክብት በላይ ከፍ ከፍ አደርጋለሁ፥ በሰሜንም ዳርቻ በመሰብሰቢያ ተራራ ላይ እቀመጣለሁ፤ ከዳመናዎች ከፍታ በላይ ዐርጋለሁ፥ በልዑልም እመሰላለሁ አልህ።
ነገር ግን ወደ ሲኦል ወደ ጕድጓዱም ጥልቅ ትወርዳለህ። የሚያዩህ ይመለከቱሃልና። በውኑ ምድርን ያንቀጠቀጠ፥ መንግሥታትንም ያናወጠ፥ ዓለሙን ሁሉ ባድማ ያደረገ፥ ከተሞችንም ያፈረሰ ምርከኞቹንም ወደ ቤታቸው ያልሰደደ ሰው ይህ ነውን? ብለው ያስተውሉሃል።" <ትንቢተ=">ትንቢተ" ኢሳያስ="ኢሳያስ" 14፥12-17=">12-17">
እንግሊዛውያኑ የተወዳጅ ሙዚቃ ቡድን 'ቢትልስ' እንደ አብዛኛዎቹ የዓለት ሙዚቃ ቡድኖች የሉሲፈር አምላኪዎች ነበሩ። በዘመናችንም የዓለም አቀፋ የሙዚቃ ኢንዱስትሪ ያመረታቸው እንደ ማይክል ጃክሰን፣ ካንዬ ዌስት፣ ቢዮንሴና ሪሃና የመሳሰሉት አጥቢያ "ክዋክብት" ሉሲፈርን ነው በማገልገል ላይ የሚገኙት። በአጋናንት እንደተያዙና ሉሲፈርንም እንደሚያመልኩ አብዛኞቹ ታዋቂ የሙዚቃና ኪነጥበብ ሰዎች በግልጽ የሚታዩበት ፡ እራሳቸውም ደፍረው የሚናገሩበት ጊዜ ላይ ደርሰናል። ሪሐና ለዝና ስትል "ነፍሴን ሸጫለሁ" ብላ በግልጽ ትናገራለች፣ ሊሲፈራውያኑንና ኢሉሚናቲዎችንም በተለያዩ ሥራዎቿ በይፋ ታንጸባርቃለች። የብሪታኒያዋ ንግሥት ኤልሳቤጥ የ “ዳይመንድ / አልማዝ ኢዮቢልዮ በተከበረበትና የለንደኑ የኦሎምፒክ ጨዋታዎች በተካሄዱበት በ 2012 ዓ.ም፡ ሪሐና፡ "ዳይመንድስ" የሚለውን ተወዳጅና ማራኪ ዘፈኗን አወጣች። በዚህም ዘፈኗ “We're Beautiful Like Diamonds in the Sky” ብላ እያቅራራች ሉሲፈርን በግልጽ ታሞግሳለች። ሙሉው ግጥም እዚህ። ሪሐና እና ቢዮንሴ በኢትዮጵያ ሚለኒየም ወደ ኢትዮጵያ መሄዳቸው፡ በተለይ ቢዮንሴ ከአቡነ ጳውሎስ ጋር መገናኘቷ አጋጣሚ አይመስለኝም። የሴቶች እግርኳስ ቡድናችን ተጫዋቶችስ እንዴት "ሉሲዎች" የሚል ቅጽል ስም ሊይይዙ ቻሉ?
የመጨረሻዎቹ ቀናት ላይ እንገኛለን። ብዙ የታሪክ ዘመናትን ያሳለፍን፣ ተወዳዳሪ የሌለውን የስቃይ ፈተና ያየን እኛ ኢትዮጵያውያን እስከ መጨረሻው ልንዘልቅ ጥቂት ነው የቀረን። የፈለገው ቢሆን፣ ብንራብና ብንጠማም አላፊውን ዓለም ለመውረስ ስንል ነፍሳችንን አሳልፈን መስጠት የለብንም፡ ያለን አንድ ትልቅ ኃብት እርሱ ነውና። ስለዚህ ህጻናቶቻችንን፣ ሴቶቻችን ከነጣቂው ሉሲፈር ከነፍሰ-በላው አውሬ ነቅተን ጠንክረን ልንጠብቅ ይገባናል፡ ለዚህም ኢትዮጵያኛው እምነታችን ጦራችን፡ ፍቅር ደግሞ ጋሻችን ናቸው።
ጌታችን የሚያበራ መለኮታዊ ወርቅ፡ የሚያበራ መለኮታዊ ፋና፣ አንጸባራቂ መለኮታዊ ፀሐይ እና ጠላታችንን የሚያቃጥል መለኮታዊ እሳት ነው።
የሚከተሉት ጠቃሚ መረጃዎች ጊዜውን እንድንዋጅ ይረዱናል የሚል እምነት አለኝ።




Comments