top of page

ወርቃማ መሠረቷ በተቀደሱት ተራሮች ላይ ነው

እንኳን ደስ ያለን እህት መሠረት ደፋር!

ድንቅ አሯሯጥ፣ ማርያማዊ የምስጋና አሰጣጥ ወቅት

ስሜታዊ የሽልማት ስነሥርዓት

እንዳንቺ ለ5ሺ የለፋ ማን አለ!


በእመቤታችን የፍልሰታ ጾም ጸሎቷ ድሉን ሰጠሽ ፤ እንዳንች ላሰባት እጹብ ድንቅ ድል፤ ለረጅም ጊዜ የሚቆይ ብርታትን እንደምትሰጥ ለዓለም አስመሰከርሽ። የጥሩነሽም የመዳብ መዳይ ጥሩ ነው፤ በወርቅ ላይ መዳብ ወርቅ ነው።

እህታችንን አበባን ዲይብሎስ አታለላት፤ ከዳተኛዋን ጀማል ልኮ ፍዝዝ እንድትል አደረጋት ፣ በማርያም ስለቀናም ቱርኮቹን እንድትረዳ ጀማልን ፊቷ ላይ ቸክሎ ውዥንብር ፈጠረባት፤ ከ500 ሜትር በኋላ እባባዊ ተንኮሉ ግልጥ ብሎ ይታይ ነበር፤ የራሷን ፍጥነት ተከትላ መሮጥ ነበረባት። ግን ምንም አይደለም፡ ሌላ ጊዜ በተሻለ ሁኔታ ትሞክራለች፡ ሌሎቻችሁ እንዳትታለሉ ሁልጊዜ ነቃ በሉ፡ ነገሮች ባጭር ጊዜ ውስጥ ሊለዋወጡ እንደሚችሉ ከዛሬው ጉድ ተማሩ፡ የእባብን መንሸላሸል እያያችሁ ሁልጊዜ ከበስተኋላችሁ እንዲቀር አድርጉ፡ ነገሩ ሩጫ ብቻ፡ ስፖርት ብቻ እንዳልሆነ ተገንዘቡ።

___________________________________________

 
 
 

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page