ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው ታቦት ከጅቡቲ በተዓምራት ተመለሰAbraham EnochApr 27, 20141 min readየእስራኤልን አምላክ ታቦት ስደዱአት፤ እኛንና ሕዝባችንን እንዳትገድል በስፍራዋ ትቀመጥ፡፡<1ኛ=">ኛ" ሳሙ.=">." 5፤=">፤" 12=">">1ከአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የተሰረቀው የመድኀኔዓለም ታቦት ጅቡቲ ውስጥ ለ17 ዓመታት በአንድ ግለሰብ ቤት ተደብቆ ከቆየበት ተዓምራቱን በመግለጡ በተደናገጠው ቤተሰብ ጠቋሚነት፤ ጅቡቲ ለሚገኘው ለምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስቲያን በማስረከብ ሚያዚያ 17 ቀን 2006 ዓ.ም. ወደ ኢትዮጵያ ተመልሷል፡፡“በ1938 ዓ.ም. የተቀረጸውና በአፄ ዋሻ ማርያም ገዳም የነበረው የመድኀኔዓለም ታቦት ሐምሌ 28 ቀን 1989 ዓ.ም. የቤተ ክርስቲያኑን በርና መስኮት ተሰብሮ መሰረቁን ለወረዳው ቤተ ክህነትና ለፖሊስ በወቅቱ አሳውቀን ነበር፡፡ ለማፈላለግ ያደረግነው ጥረት ሁሉ መና ሆኖብን ቆይቷል፡፡ እግዚአብሔር በወደደ ጊዜ ወደ ቤቱ ይመለስ ዘንድ ፈቀደ፡፡” ይላሉ የገዳሙ አስተዳዳሪ ቄስ ኃይለ ጊዮርጊስ መኮንን፡፡ጅቡቲ እንዴት እንደተወሰደ እስካሁን በግልጽ የታወቀ ነገር እንደሌለ የሚገልጹት የጅቡቲ ምሥራቀ ጸሐይ ቅዱስ ገብርኤል ቤተ ክርስስቲያን አስተዳዳሪ ቆሞስ አባ ዮናስ መልከ ጼዲቅ “ታቦቱ በግለሰቡ ቤት ታላቅ ተዓምራትን ነው ያደረገው፡፡ በቤቱ ውስጥ ደብቆ ያስቀመጠው ግለስብ ሚስት ስታብድ ልጁ ሞቶበታል፡፡ በዚህ የተደናገጠው ሌላው የሰውየው ልጅ በቤታቸው ውስጥ ታቦት እንዳለና ወደ ቤተ ክርስቲያን እንዲወሰድ ባቀረበው ጥያቄ መሠረት ጉዳዩን በመከታተል ከጠቅላይ ቤተ ክህነት፤ ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፤ በጅቡቲ የኢትዮጵያ ኤምባሲና ከሌሎችም ጋር መረጃ በመለዋወጥ ወደ ኢትዮጵያ ለማምጣት ችለናል” ብለዋል፡፡ምንጭ__
Fire at The Church of Saint Mary The Virgin in Luxor Egypt – Huge Explosion Inside the Church ባለፈው ቅዳሜ ዕለት (ዮሐንስ እና ማርቆስ) በ ግብፅ ሉክሶር/ቴቤን የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ፥ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ነበር
Comments