ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን ፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ
- Abraham Enoch
- Jan 31, 2021
- 1 min read
https://youtu.be/pFV88DX2wLM
በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች።
<መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፭>መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፳፭>
፩ አቤቱ፥ እኔ በየውሃቴ ሄጃለሁና ፍረድልኝ፤ በእግዚአብሔርም አምኛለሁና አልናወጥም።
፪ አቤቱ፥ ፍተነኝ መርምረኝም፤ ኵላሊቴንና ልቤን ፍተን።
፫ ምሕረትህ በዓይኔ ፊት ነውና፥ በእውነትህም ተመላለስሁ።
፬ በከንቱ ሸንጎ አልተቀመጥሁም፥ ከዓመፀኞችም ጋር አልገባሁም።
፭ የክፉዎችን ማኅበር ጠላሁ፥ ከዝንጉዎችም ጋር አልቀመጥም።
፮ እጆቼን በንጽሕና አጥባለሁ፤ አቤቱ፥ መሠዊያህን እዞራለሁ፥
፯ የምስጋናን ድምፅ እሰማ ዘንድ፥ ተአምራትህንም ሁሉ እነግር ዘንድ።
፰ አቤቱ፥ የቤትህን ስፍራ የክብርህንም ማደሪያ ቦታ ወደድሁ።
፱ ከኃጢአተኞች ጋር ነፍሴን፥ ከደም ሰዎችም ጋር ሕይወቴን አታጥፋ።
፲ በእጃቸው ተንኰል አለባቸው፥ ቀኛቸውም መማለጃ ተሞልታለች።
፲፩ እኔ ግን በየውሃቴ ሄጃለሁ፤ አድነኝ ማረኝም።
፲፪ እግሮቼ በቅንነት ቆመዋልና፤ አቤቱ፥ በማኅበር አመሰግንሃለሁ።
______________________________
Comments