top of page

እንቁጣጣሽ መልካም አዲስ ፳፻፲፯ ዓመት፤ የፍትሕ እና ተጠያቂነት ዘመነ ማቴዎስ


https://youtu.be/Z-a_Fqrq1m0

እንቁጣጣሽ መልካም አዲስ ፳፻፲፯ ዓመት፤ ዘመነ ማቴዎስ

ዘመን አልፎ ዘመን ሲተካ ሳር ቅጠሉ ሁሉ ሲፈካ ዝናም በሙቀት ሊተካ ብርሃን ጨለማን ሲተካ እንቁጣጣሽ፡ እንቁጣጣሽ!!

ደህና ጊዜን ይዘሽ ደግሞ ደግሞ ያምጣሽ። እርቅ ነው ፍቅር ነው ለኛ አዲስ ዘመን፡ የሚታረቀውን እናቀናለን፡ አረሙን እንነቅላለን። ፳፻፲፯ የውዲቷ የአክሱማዊቷ ኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያፍሩበት፡ ልዩ ዘመን ሕዝባችን የሚነቃበት።

እንቁጣጣሽ በያመቱ ያምጣሽ! መልካም አዲስ አመት!

መልካም አዲስ ፳፻፲፯ -- Happy Ethiopian New 2017 Year!

መጭው የ ፳፻፲፯ አመት፡ የሰላም፣ የፍትሕ፣ የፍርድ፣ የፍቅር፣ የጤና እና የደስታ ዘመን ይሁንልን !!!

ኢትዮጵያ በእግዚአብሔር የመሰረተችና በቅዱሳን ቃል ኪዳን የተጠበቀች፤ ከሁል በላይ ደግሞ የእመቤታችን አስራት አገር ስለሆነች እንኳን በአገር ዉስጥ ለጥፋቷ የተሰለፉ አይደለም፤ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የዉጭ መንግሥታት በሙሉ በእግዚአብሔር ቁጣ ይጠፋሉ፤ ከምድር ይጠረጋሉ። እርሷ ግን በእግዚአብሔር መንግሥትነቷ እስከ ዓለም ፍጻሜ ድረስ ትቆያለች። ታዲያ አሁን ቢሆን “የአዲሲቷ ኢትዮጵያ መሪዎች ነን” እያሉ በኢትዮጵያና በኢትዮጵያዊነት ላይ የሚያላግጡ ሆኑ እርሷን ለማጥፋት የተሰለፉ የተለያዩ ቡድኖችና ድርጅቶች እንዲሁም መንግሥታትና ግለሰቦች ዛሬ ነገ ሳይሉ በእዉነተኛ ንስሐ ለእግዚአብሔር እጃቸዉን ቢሰጡና ወደማንነታቸዉ ወይንም ወደ ኢትዮጵያዊነታቸዉ ቢመለሱ የሚበጃቸዉ እንደሆነ በዚሁ አጋጣሚ መልእክቱን አቀርባለሁ።

ኢትዮጵያ እንኳን ዜጎቿን “ኢትዮጵያዉያን ነን” የሚሉትን ቀርቶ የዓለምን ሕዝብ ትመራለች ብንላችሁ “ኡ! !“ ልትሉ ስለምትችሉ የንስሐ እድሜ ካገኛችሁ ተፈጽሞ እንደምታዩ እንነግራችኋለን።

♱ ንቡረ እድ ኤርምያስ ከበደ ወልደ ኢየሱስ ♱

_______

_______

 
 
 

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page