ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን መገሰጽና ለእነርሱ መጸለይም ይገባናልAbraham EnochFeb 24, 20132 min readዳኛው ፈራጁ ሁሉን ነገር የሚያየው እርሱ ንጉሡ ክርስቶስ ብቻ ነው!"በእግዚአብሔርም ቍጣ ቀን ብራቸውና ወርቃቸው ሊያድናቸው አይችልም፤ እርሱም በምድር የሚኖሩትን ሁሉ ፈጥኖ ይጨርሳቸዋልና ምድር ሁሉ በቅንዓቱ እሳት ትበላለች።”<ትንቢተ=">ትንቢተ" ሶፎንያስ.1፥18=">">ባዕዳውያኑ የአገራችን ጠላቶች ምንም ሳናደርጋቸው፤ ሳንደርስባቸው በሕዝባችን ላይ ያደረሱት በደል በዓይነቱ በጣም አስከፊ በመጠኑም እጅግ በጣም ከፍ ያለ ነው፡ ለሃሳብ እንኳ የሚያንገፈግፍ ነው። አንመኝላቸውም፡ ግን የፍትህ አምላክ፡ ኅያሉ ፈጣሪያችን መቅሰፍቱን ያወርድባቸዋል፤ ሌላ አማራጭም ያለ አይመስልም።በመጪዎቹ የጾምና የጸሎት ቀናት እንድንድንና እንዲድኑ ልዩውን ጸሉት ልናደርስ ይገባናል። በማወቅም ሆነ ባለማወቅም በክህደታዊ መንገድ ከጠላቶች ጋር በመመሳጠርና በመተባበር ወንድሞቹን፣ እህቶቹን እንዲሁም ልጆቹን ለአውሬው አሳልፎ ለሚሰጠው "ኢትዮጵያዊ" ጊዜው ሳይረፍድ እንጸልይላቸው፤ማንነታቸውን ክደው የክርስቶስ አምላክን ልብ ለሚያቆስሉት፡ለተታለሉት የባዕዳውያን እምነት ተከታዮች ሁሉ እንዲድኑ ፀሎት እናድርስላቸውየክርስቶስን ደናግልት ህፃናት ለባእዳዊ ሰዶማውያን ለሚያስረክቡት እንዲድኑ እንጸልይላቸውየክርስቶስ ልጆች እንዳይበዙ የእህቶቻችንን ማሕፀን ለሚመርዙት ጨካኝ ውገኖች እንዲድኑ እንጸልይላቸው በክርስቶስ ስም የተጠመቁትን እህቶቻችንን ለአረማውያኑ ጣኦት-አምላኪ ባዕዳን አሳልፈው ለሚሰጡት የዘመኑ ጂፋሮች እንዲድኑ እንጸልይላቸውየክርስቶስን ገናናነትና ክብር ለመቀነስ የናዝሬትን፣ የደብረ ዘይትንና የመሳሰሉትን የኢትዮጵያ ቦታዎች ስም በዘፈቃድ ለሚቀይሩት ምስጋና-ቢሶች እንዲድኑ እንጸልይላቸውውጩ አገር ሆነው፡ ቸሩ እግዚአብሔር የሰጣቸውን ጸጋ ቸል በማለት እራሳቸውን በስንፍና የስድብና ጥላቻ ማዕበል ውስጥ ለከተቱና ወገናቸውንና ቅድስት ቤተክርስቲያናቸውን በድፍረትና በትዕቢት ለሚያዋርዱት እንዲድኑ ጸሎቱን እናድርስላቸው።"ወላጆችም ስንኳ ወንድሞችም ዘመዶችም ወዳጆችም አሳልፈው ይሰጡአችኋል፥ ከእናንተም አንዳንዱን ይገድላሉ"<ሉቃስ=">ሉቃስ" 21:16=">21:16">ኒፈሌያዊ የደመና መጋረጃዎች ባገራችን ሰማያት ላይ ተዘርግተዋል፡ ነገር ግን የጽዮን ልጆች በእግዚአብሔር ብርኃን የተከበቡ፡ በፍቅሩ የታጠሩ ናቸውና የእርሱ ኃይል ይጠብቃቸዋል፡ የሚያሸነፋቸውም ኅይል የለም። የቃልኪዳኑ ልጆች ያሉበት ቦታ ሁሉ አምላካችን ስላለ ሁሉ ነገር ጥሩ ነው፡ ቸር ነው፤ በቤቱ ለዘላለም ለመኖር ተመርጠዋልና።የቅዱሳን አምላክ ቸሩ እግዚአብሔር ነብዩ ዮናስን፡ ልክ እንደ ክርስቶስ፡ ሦስት ቀን እና ሦስት ሌሊት በአሣ ሆድ አሳድሮ ከክፉ ነገር ሁሉ ጠብቆ እንዳዳነው እኛንም ከመጥፎ ነገር ይከላከለን ከመቅሰፍት ይጠብቀን። አሜን!ትንቢተ ዮናስ ምዕራፍ አራትየተናገረው ቃል ስላልተፈጸመዮናስ ተቆጥቶ እያጕረመረመእንደዚህ እያለ ጸለየ ወደ አምላክእኔን መጀመሪያ ነነዌ ለመላክአስበህ ብታዘኝ ይህንኑ ዐውቄወደ ተርሴስ ልሄድ ጠፋሁ ተደብቄምሕረትህ የበዛ መሓሪና ታጋሽበደል የምትረሳ ከቍጣ ተመላሽየቍጣህን ያህል ምሕረትህ የጠናመሆንክን ጥንቱንም እኔ ዐውቃለሁናእኔን ግን ግደለኝ ልሙት ልቀበርሐሰት ተናግሬ የማይሆን ነገርአልፈልግምና ቆሜ ለመኖርክከተማ ወጥቶ በምሥራቅ በኩልከወደ ዳር ሆኖ ነነነዌን ሊያስተውልምን እንደሚያገኛት ለማየት ዮናስሠርቶ ተቀመጠ አንድ ትንሽ ዳስእግዜር በጥበቡ አንድ ቅል አብቅሎቅሉም አደገና ከፍ ከፍ ብሎየዮናስ ራሱ እንዲያገኝ ጥላለፀሓዩ ንዳድ ሆነለት ከለላበዚህ በቅል አገር ዮናስን ደስ አለውእንዲህ ቶሎ ደርሶ ስላገለገለውእግዜር በማግሥቱ ጧት በማለዳቅል የሚበላ ትል ፈጣሪ አሰናዳትሉ ቅሉን በልቶ በፍጥነት ደረቀፀሓይ ወጣችና ግዜው በጣም ሞቀእግዜር አዘዘና ትኩስ ነፋስ መጣየሚከለልበት መጠጊያ ስላጣቅሉ ደረቀና ንዳድ ቢያቃጥለውዮናስ ተበሳጭቶ ላምላክ እንዲህ አለውእንደዚህስ ሆኜ ቆሜ ከምኖርእባክህ ግደለኝ ልሙት ለቀበርደረቀብኝ ብለህ ይህን ቅል ለማጣትእውን ይገባል ወይ ያንተ አሁን መቆጣት?ብሎ እግዜር ቢጠይቅ መለሰ ዮናስበንዴቴ ብዛት እስክሞት ድረስአዎን ይገባኛል መናደድ መጤስእግዜርም መለሰ ለምን ጠፋ ስትልይህ ያልለፋህበት ያልደከምህበት ቅልአንተ ስትናደድ ፈጥሬአት እኔማ ሳጠፋት ሳፈርሳት ነነዌን ከተማመቶ ሓያ ሺህ ነው የሕዝብዋ ብዛትለምን ትቆጣለህ እኔ ባዝንለትብሎ በምሳሌ ሲያስተምር ይቅርታለዮናስ ነገረው የምሕረቱ ጌታለእግዚአብሔር ቸርነት ምስጋና ይድረስከምዕራፍ 1-3 PDF እዚህ__
Fire at The Church of Saint Mary The Virgin in Luxor Egypt – Huge Explosion Inside the Church ባለፈው ቅዳሜ ዕለት (ዮሐንስ እና ማርቆስ) በ ግብፅ ሉክሶር/ቴቤን የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ፥ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ነበር
Comments