አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት
- Abraham Enoch
- Oct 27, 2024
- 1 min read
https://youtu.be/7mNd7TUrIBs
💭 ዛሬ በሃገራችን እየሆነ ያለው ይህ ነው፤ በእውነት የእግዚአብሔር ቃል በጣም የሚያስደንቅ ነው!
❖<መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፰ / ፸፱>መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፸፰ / ፸፱>❖
፩ አቤቱ፥ አሕዛብ ወደ ርስትህ ገቡ፤ የቅድስናህንም መቅደስ አረከሱ፥ ኢየሩሳሌምንም እንደ መደብ አደረጉአት ፪ የባሪያዎችህንም በድኖች/ሬሳ ለሰማይ ወፎች መብል አደረጉ፣ የጻድቃንህንም ሥራ ለምድር አራዊት፤ ፫ ደማቸውንም በኢየሩሳሌም ዙሪያ፣ እንደ ውሃ አፈሰሱ፤ የሚቀብራቸውም አጡ። ፬ ለጎረቤቶቻችንም ስድብ ሆንን፥ በዙሪያችንም ላሉ ሣቅና ዘበት። ፭ አቤቱ፥ እስከ መቼ ለዘላለም ትቈጣለህ? ቅንዓትህም እንደ እሳት ይነድዳል? ፮ ስምህን በማይጠሩ መንግሥታት ላይ በማያውቁህም አሕዛብ ላይ መዓትህን አፍስስ፤ ፯ ያዕቆብን በልተውታልና፥ ስፍራውንም ባድማ አድርገዋልና። ፰ የቀደመውን በደላችንን አታስብብን፥ ምሕረትህ በቶሎ ታግኘን፥ እጅግ ተቸግረናልና። ፱ አምላካችንና መድኃኒታችን ሆይ፥ እርዳን፤ ስለ ስምህ ክብር፥ አቤቱ፥ ታደገን፥ ስለ ስምህም ኃጢአታችንን አስተሰርይልን። ፲ አሕዛብ፥ አምላካቸው ወዴት ነው? እንዳይሉ፥ የፈሰሰውን የባሪያዎችህን ደም በቀል በዓይኖቻችን ፊት አሕዛብ ያወቁ፤ ፲፩ የእስረኞች ጩኸት ወደ ፊትህ ይግባ፤ እንደ ክንድህም ታላቅነት ሊገደሉ የተፈረደባቸውን አድን። ፲፪ አቤቱ፥ የተዘባበቱብህን መዘባበታቸውን ለጎረቤቶቻችን ሰባት እጥፍ በብብታቸው ክፈላቸው። ፲፫ እኛ ሕዝብህ ግን፥ የማሰማርያህም በጎች፥ ለዘላለም እናመሰግንሃለን፤ ለልጅ ልጅም ምስጋናህን እንናገራለን።
_______
_______
Comments