አርቲስት ሰገን ይፍጠር የትግራይ ሕዝብ ስለደረሰበት ግፍና ሰቆቃ
- Abraham Enoch
- Jan 19, 2021
- 1 min read
https://youtu.be/8foglG2VEBY
ዛሬ ቀኑን ሙሉ በጥልቁ ሳሰላስልባቸው የነበሩት ጥያቄዎች፤ “በተለይ ኦሮሞ እና አማራ በትግራይ ሕዝብ ላይ ምን ያህል ጥላቻ ቢኖራቸው ነው በዘመነ ኮሮና፣ በዘመነ አንበጣ “እንኩ!” ከማለት በቀር ምንም ባላደረጓቸው በትግራይ ኢትዮጵያውያን ወገኖቻቸው ላይ ተናበው ጦርነት ለማወጅ የደፈሩት? የሕዳር ጽዮንን፣ ገናን እና ጥምቀትን እንኳን እስከማያከብሩ ድረስ ጭካኔ የተሞላበት ፋሺስታዊ ተግባር እየተፈጸመባቸው፣ አረጋውያን እና ሕፃናት እየተሰደዱ፣ እየተራቡና እየተገደሉ እንዴት ጸጥ ብለው ለብቻቸው በዓል ለማክበር ተቻላቸው? የሚሉት ጥያቄዎች ናቸው። ከዚህ የበለጠ ጭካኔ እኮ የለም!ይህን የጥቃት ዘመቻ በመደገፋቸው በሁለቱ ሕዝቦች ላይ የሚመጣባቸው መቅሰፍት ደግሞ ገና ካሁኑ በጣም ረብሾኛል። ፈሪሃ እግዚአብሔር ያላቸው ሆነው በፍጹም አይታዩኝም፤ ለንስሐ የሚያበቃ ስራ እንኳን ለመስራት ጥረትም፣ ዝግጁነትም ብቃትም የላቸውም ማለት እኮ ነው።
ይህ ዲያብሎሳዊ ድርጊት እኮ ናዚው ሂትለር ከሰማኒያ ዓመታት በፊት በሩሲያውያኑ ላይ ከፈጸመው ኢ-ሰብዓዊ ተግባር ጋር እጅግ በጣም ተመሳሳይ ነው። ልብ እንበል፤ ግራኝ ትግራይን ማገድ፣ መተንኮስ፣ ለወረርሽኝ በሽታ፣ ለአንበጣ፣ ለረሃብ ማጋለጡን የጀመረው ከሁለት ዓመት ተኩል በፊት ጀምሮ ነበር። የሂትለርን ፍኖተ ካርታ ይዞ ጥቃቱን በመፈጸም ላይ ካለው አውሬ ጎን ቆመው “በለው! ግደለው! ግፋበት!” እያሉ ወደ ጥልቁ እየወረዱ እኮ ነው ወገኖቼ። እንዴት ይሄን መገንዘብ ተሳናቸው?
______________________________
Comments