top of page

ችቦ በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው


https://youtu.be/guQWSwJrBF8

😇 ጌታችን ምሥጢረ መለኮቱን ለገለጠበት ለበዓለ ደብረ ታቦር እንኳን አደረሰን!

☀️ የቡሄው ብርሃን፣ የቡሄው ☀️ ብርሃን ለእኛ መጣልን ☀️

ጌታችን አምላካችንና መድኀኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በደብረ ታቦር ብርሃነ መለኮቱን፣ ክብረ መንግሥቱን መግለጡን በማሰብ በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ ቀን በዓሉ በድምቀት ይከበራል፡፡

ይህ በዓል በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ዘንድ ‹‹ቡሄ›› በመባል ይታወቃል፡፡ ቡሄ ማለት /መላጣ ፣ ገላጣ/ ማለት ነው፡፡ በአገራችን ክረምቱ፣ አፈናው ተወግዶ የብርሃን ወገግታ የሚታይበት በዚሁ በዓል አካባቢ ስለኾነ ‹‹ቡሄ›› እንደ ተባለ ይገመታል፡፡ ጌታችን ብርሃነ መለኮቱን የገለጠበት፣ ብርሃን የታየበት፣ ድምፀ መለኮት የተሰማበትና ችቦ የሚበራበት ዕለት ስለ ኾነ ደብረ ታቦር የብርሃን ወይም የቡሄ በዓል ይባላል፡፡

ቡሄ ሲመጣ የክረምቱ ጨለማነት አልፎ ወደ ብርሃን፣ ወደ ጥቢ የሚያመራበት፣ ወደ መፀው የሚገባበት፣ ወገግታ የሚታይበት፣ ሰማይ ከጭጋጋማነት ወደ ብሩህነት የሚለወጥበት፣ የሚሸጋገርበት ወቅት በመኾኑ ከቡሄ በኋላ የጠነከረ ክረምት አይኖርም፡፡ ‹‹ቡሄ ከዋለ የለም ክረምት፤ ዶሮ ከጮኸ የለም ሌሊት›› እንዲሉ፡፡

በአንዳንድ የአገራችን አካባቢዎች የቡሄ ዕለት ማታ ምእመናን ችቦ ያበራሉ፡፡ ይህም በደብረ ታቦር ለታየው ብርሃነ መለኮት ምሳሌ ነው።

_______

_______

Comments


bottom of page