ቅድስት ሐና ማርያም ቤ/ክርስቲያንና ድንቅ ዛፎቿ
- Abraham Enoch
- May 19, 2013
- 3 min read
በዛሬዋ የሐና ማርያም ዕለት አዲስ አበባ ነፋስ ስልክ ላፍቶ ስለምትገኛዋ ቅድስት ሐና ማርያም ይህችን ቪዲዮ በማቅረብ አንዳንድ ትዝታዎችን ልቀስቅስ። እንኳን አደረሰን!
የቅድስት ሐና ማርያም ቤተክርስቲያን በብዙዎቻችን ዘንድ በሚገባ የማትታወቅ፡ ነገር ግን፡ በእውነት፡ አዲስ አበባ ካየኋቸው ዓብያት ክርስቲያናት መካከል በጣም ከሚያማምሩት መካከል ልትመደብ የሚገባት ቆንጆ ቤተክርስቲያን ነች።
እ
.
ኢ
.
አ በ
1920
ዎቹ አመታት በታላቋ ንግሥት ነገሥታችን ዘውዲቱ ዘመን የተገነባችው ይህች ቤተክርስቲያን ኮረብታማ በሆነ አቀማመጧ እጹብ ድንቅ የሆነ ቦታ ይዛለች። በዚያ ዘመን ከ
100
ዓመታት በፊት፤ ማለትም አካባቢዋ ገና የገጠራማ ባሕርይ ይዛና በጫካ ብቻ ተከብባ በነበረችበት ዘመን ንግሥቲቷ የቅድስት ሐና ማርያምን ቤተክርስቲያን ሕንፃ መሠረት ሲያስቀምጡ፡
"
ወደፊት ይህች አካባቢ የአዲስ አበባ መኻል ከተማ ትሆናለች
"
በማለት ትንቢት ተናግረው ነበር። እንዳሉትም፡ ቀስ በቅስ በማደግ ላይ የምትገኘው የሐና ማርያም አካባቢ እየሰፋች ለመጣችው የአዲስ አበባ ከተማችን ባሁኑ ጊዜ መኻከለኛ የሆነ አቀማመጥ አላት። ይህም በጣም የሚገርም ነው
!
እዚህኛው ቪዲዮ ላይ በከፊል የሚታዬው የሐና ማርያም ቤተክርስቲያን አንጋፋ እና ጥንታዊ ዛፍ አካባቢ ሆኜ
(
በተከታዩ ቪዲዮ አቀርበዋለሁ
)
ራቅ ብሎ የሚገኘውን ጋራ ሸንተረር ስቃኝ ይሰማኝ የነበረው የመንፈስ መረጋጋትና ሰላም እጅግ በጣም ጥልቅ ነበር። ጸጥታውና መረጋጋቱ የከተማው ግርግርና ጫጫታ ከሚፈጥረው ሁከት በጣም ፈዋሽ ሆኖ ነው ያገኘሁት።
ቀጥሎ በእንግሊዝኛ የቀረበው ሳይንሳዊ ጥናት ዛፍን መጠጋት ወይም ማቀፍ አንድን ግለሰብ ጤናማ እንደሚያደርገው ባለመነጽሩ ሊቃውን ሳይቀሩ እንደሚመሰክሩ ነው የሚገልጸው። ታዲያ ዓብያተ ክርስቲያናቶቻችንና ገዳማቶቻችን በዛፎችና ልዩ ልዩ በሆኑ ዕፀዋት መከበባቸውና ምዕመናኑም እነርሱን በመጠጋት ከተፈጥሮና ከፈጣሪያቸው ጋር አንድ ለመሆን የጸሎት ጊዚያቸውን እዚያ በትጋት ማሳለፋቸው ኃይል ሰጪው የልዑል እግዚአብሔር ቅዱስ መንፈስ የት እንደሚገኝ በውል የሚያረጋግጥ አይደለምን
?!
መንፈሳዊ ውድቀት ባራቆቷት፤መንፈሳዊው ጦርነት እየተጧጧፈ በመጣበት ዘመናችን እነዚህ ዓብያተክርስቲያናቶቻችንና ገዳማቶቻችን ከምናስበው በላይ ውድ የሆነ ሚና ይጫወታሉ ስለዚህ ልንጠብቃቸውና ልንንከባከባቸው ይገባናል።




Comments