ቃኤል፤ ለምን ተናደድህ? ከአህዛብና መናፍቅ ጋር ሆነህ ወንድምህ አቤልን ለምን ገደልከው?
- Abraham Enoch
- Jan 31, 2021
- 1 min read
https://youtu.be/0ko3zIJ-IDw
በግፍ የገደልከው የወንድምህ ደም ወደላይ ይጮሃል!!!
ባብዛኛው ነገር100% ትክክል ነው! ይገርማል፤ ሰሞኑን ተደጋግሞ ይታየኝና ይሰማኝ የነበረው ልክ ይህ ነበር። የአባ ሰረቀ ብርሃንን ቪዲዮዎችን ለመጀመሪያ ጊዜ ማየቴና መስማቴ ነው፤ ከብዙ “አማራ ነን” ከሚሉ ግብዝ “አባቶች” የተሻሉ ነዎት፤ ቃለ ህይወት ያሰማልን፤ አባታችን! እንግዲህ ከንቱዎቹ የአማራ ልሂቃን'እርርይ'ይበሉ! በቅናት የምታቅበዘብዛቸውን መራራዋን የእውነት ኪኒን ይዋጧት፤ ልባቸው እንደ ፈርዖን በእብሪት ደንድኗልና ለንስሐ እንኳን የሚያበቃ ትህትና እና ርህራሄ እንዴላቸው ዛሬ በተግባር አይተናቸዋል። በአክሱም ጽዮን እና በደብረ ዳሞ በሽህ የሚቆጠሩ ካህናትና ምዕመናን ሲጨፈጨፉ ጆሮ ዳባ ለብሰዋል፤ ለጥምቀት በዓል ግን በክህደትና በድፍረት የኤርትራን ባንዲራ እያውለበለቡ ሲፎክሩ ተሰምተዋል፣ ሲጨፍሩ ታይተዋል።
በትግራይ ተዋሕዷውያን ላይ እየተካሄደ ያለው ጭፍጨፋ ሦስተኛ ወሩን ይዟል፤ ነገር ግን አንድም “ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ነኝ” የሚል “አማራ” መምህር ወይንም አባት “ተው! ጦርነት ትክክል አይደለም! ወረራ፣ ዘረፋ፣ ጭፍጨፋና ግድያ ከባድ ሃጢዓት ነው” ያለ የለም፤ አንድም! እንዲያውም እነዚህ ቃኤላውያን “ከትግሬ ጎን ከምስለፍ ከሰይጣን ጋር ባብር ይሻለኛል” የሚል መርሆ ይዘውና ከአህዛብና መናፍቃን ጎን ቆመው “ያዘው! በለው! ግደለው! እርስትህን አስመልስ አክሱምንና ደብረ ዳሞን ውረስ” እያሉ አቤላውያን ትግሬዎችን ያሳድዳሉ፣ ያዘርፋሉ፣ ያስጨፈጭፋሉ! አይይ፤ የአቤል ደም እየጮኸ ነው!
<መዝሙረ=">መዝሙረ" ዳዊት="ዳዊት" ምዕራፍ="ምዕራፍ" ፲፬="፲፬</span>">
፪የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።
፫ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።
፬ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤
፭ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤
፮ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።
______________________________
댓글