top of page

ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።


https://youtu.be/NRvS5qkvptQ

አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

እነ ግራኝ አረመኔዎቹ በረሃብና በጥይት እየቀጡት ስላሉት ስለ ትግራይ ሕዝብ መከራ እና ጩኸት እግዚአብሔር እየተነሣ ነው። በዚህ ከንቱ ትውልድ የተደገፈው የግራኝ ሠራዊት ጽላተ ሙሴን ለመስረቅ ወደ አክሱም አመራ፤ ነገር ገን መንፈስ ቅዱስ የመራቸው የትግራይ ተዋሕዶ አገልጋዮች ጽላቱን አስቀድመው ወደተፈቀደለት ቦታ ወስደውት ነበር። ይህን የተገነዘበው የግራኝ ሠራዊት በብስጭት፣ በቁጣና በበቀል ከሰባት መቶ ሃምሳ ስምንት እስከ ስህ ም ዕመናንን አክሱም ጽዮን ቤተ ክርስቲያን ፊት ገደላቸው፤ ለሰማዕትነት አበቃቸው። አሁን ስድስት ሚሊየን ተዋሕዷውያንን በረሃብ ለመቅጣት ምግብና ውሃ እንዳይደርሳቸው በመከልከል ላይ ነው። በተቀረው የኢትዮጵያ ግዛቶች የሚኖረው አሳፋሪና ከንቱ ትውልድ ዛሬም ዝምታውን መርጧል፤ አንድነትንና ርህራሄን ሳያሳይ በቀን ሦስት ጊዜ እየበላ በግድየለሽነት መኖሩን ቀጥሏል። ስድስት ሚሊየን የትግራይን ሕዝብ ከረሃብ ለማዳን የአዲስ አበባ ነዋሪ “ጦርነቱን አቁሙ፣ እርዳታውን ስጡ!” የሚል ታላቅ ሰልፍ ማድረግ ቢችል ብቻ በቂ ነበር፤ ግን “እኔ ብቻ! የኔ ብቻ! ኬኛ!” የሚል ስለሆነ እና የትግራይ ሕዝብ እንዲያልቅ ስለፈለገ ይህን አያደርገውም። ስለዚህ በእሳት ቢጠራረግና ወደ ሲዖል ቢወርድ አላዝንም!

በሦስት ሽህ ዓመት ስንት ጥቃትና ጦርነት አሳልፋ ለዚህ የበቃችውን አክሱም ጽዮንን እነ ግራኝ አህመድ ቀዳማዊና ዮዲት ጉዲት እንኳን ይህን ያህል አልደፈሯትም ነበር፤ አሁን በዘመናችን የታየው ድፍረትና ጥቃት የሚነግረን ይህ ትውልድ ምን ያህል ከንቱ መሆኑን ነው።

<መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩>መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፩>

፩ አቤቱ፥ አድነኝ፤ ደግ ሰው አልቆአልና፥ ከሰው ልጆችም መተማመን ጐድሎአልና።

፪ እርስ በርሳቸው ከንቱ ነገርን ይናገራሉ፤ በሽንገላ ከንፈር ሁለት ልብ ሆነው ይናገራሉ።

፫ የሽንገላን ከንፈሮች ሁሉ እግዚአብሔር ያጠፋቸዋል፥ ታላቅ ነገርን የምትናገረውን ምላስ፤

፬ ምላሳችንን እናበረታለን፤ ከንፈራችን የእኛ ነው፥ ጌታችን ማን ነው? የሚሉትን።

፭ ስለ ድሆች መከራ፥ ስለ ችግረኞች ጩኸት እግዚአብሔር። አሁን እነሣለሁ ይላል፤ መድኃኒትን አደርጋለሁ፥ በላዩም እገልጣለሁ።

፮ በምድር ላይ እንደ ተፈተነ ሰባት ጊዜ እንደ ተጣራ ብር። የእግዚአብሔር ቃላት የነጹ ቃላት ናቸው።

፯ አቤቱ፥ አንተ ጠብቀን፥ ከዚህችም ትውልድ ለዘላለም ታደገን።

፰ በሰው ልጆች ዘንድ ምናምንቴ ከፍ ከፍ ባለ ጊዜ ክፉዎች በዙሪያው ሁሉ ይመላለሳሉ።

<መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫>መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ ፲፫>

፩ ሰነፍ በልቡ። አምላክ የለም ይላል። በሥራቸው ረከሱ፥ ጐስቈሉ፤ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም።

፪ የሚያስተውል እግዚአብሔርንም የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ፤ እግዚአብሔር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ።

፫ ሁሉ ዐመፁ በአንድነትም ረከሱ በጎ ነገርን የሚሠራ የለም፤ አንድም ስንኳ የለም።

፬ ጕሮሮአቸው የተከፈተ መቃብር ነው፥ በምላሳቸው ሸነገሉ፤

፭ ከከንፈራቸው በታች የእባብ መርዝ አለ፤ አፋቸው መርገምንና መራራን ተሞልቶአል፤

፮ ደምን ለማፍሰስ እግራቸው ፈጣን ነው፤ ጥፋትና ጕስቍልና በመንገዳቸው አለ፥ የሰላምን መንገድ አላወቁአትምና፤ እግዚአብሔርን መፍራት በዓይናቸው ፊት የለም።

፯ ሕዝቤን እንደ እንጀራ የሚበሉ ኃጢአት የሚሠሩ ሁሉ በውኑ አያውቁምን? እግዚአብሔርንም አይጠሩትም።

፰ በዚያ በታላቅ ፍርሃት እጅግ ፈሩ፥ እግዚአብሔር በጻድቃን ትውልድ ዘንድ ነውና።

፱ የድሆችን ምክር አሳፈራችሁ፥ እግዚአብሔር ግን ተስፋቸው ነው።

፲ ከጽዮን መድኃኒትን ለእስራኤል ማን ይሰጣል? እግዚአብሔር የሕዝቡን ምርኮ በመለሰ ጊዜ፥ ያዕቆብ ደስ ይለዋል፥ እስራኤልም ሐሤት ያደርጋል።

__________________________

댓글


bottom of page