top of page

መስቀሉን ይዘን ተሸክመን እናት ኢትዮጵያን ከሉሲፈራውያኑ እና ጭፍሮቻቸው የሞትና ባርነት ቀንበር ቶሎ ነፃ እናውጣት! አለም ወደ ኑክሌር ጦርነት እየተንደረደረ ነው


https://youtu.be/tlp7mbeilqM

🔥 አለም ወደ ኑክሌር ጦርነት እየተንደረደረ ነው፤ እነሱ ኒውክሌር ሊያብላሉ ሲቆፍሩ እኛ እኮ ከተቆፈረበት በተዓምር የወጣ ግማደ መስቀሉን ይዘን ነበር ♱ ፡፡

  • የበዓል ስም ፤ በመስከረም ፲፯ ቀን የሚከበር ታላቅ በዓል ፤ የመስቀል ቅዳሴ ቤቱ።

  • ጌታ በሰቀለበት አምሳል ከንጨት ከብረት ከብር ከወርቅ ከንሓስ ከእብነ በረድ ከሌላም ማዕድን የተሠራ ቄሶች በእጃቸው የሚይዙት ክርስቲያኖች ባንገታቸው የሚያንጠለጥሉት ፤ ሴቶችም በቀሚሳቸው ላይ ያስጠልፋታል። (ያበባ መስቀል) ፤ ካበባ የተጐነጐነ እንቍጣጣሽ።

  • ግንባር ማማተቢያ ጣት የሚያርፍበት ፤ ወይም የመስቀል ምልክት ዕመት የሚደረግበት። እረኛው ላውሬ የወረወረው ደንጊያ አቶ እከሌን መስቀሉን አለው ።

  • የክርስቶስ መስቀል በኹለት ረዣዥም ዕንጨት እጅና እግሩ የተቸነከረበት ከራሱ እስከ እግሩ ወራጅ ግንድ ከቀኝ እጁ ወደ ግራ እጁ ከአግዳሚውም ግንድ ባራት ማዕዘን ተመሳቅሎ የሚታየው መስቀልኛ ዕንጨት።

  • ሐዋርያ መስቀል ትርፍ ነገር ትርፍ ቅርጽ የሌለው ልሙጥ መስቀል።

  • ሕማማተ መስቀል የክርስቶስ ልዩ ልዩ መከራው በጥፊ መመታቱ መታሠሩ መገረፉ ግንድ መሸከሙ ራቁቱን መሰቀሉ አክሊለ ሦክ የሾክ አክሊል በራሱ ላይ መቀዳጀቱ ይኸንን የመሳሰለ ልዩ ልዩ መከራው ሕማማተ መስቀል ይባላል።

  • ልዩ ልዩ መስቀል የመስቀል ዐይነት ኹኖ በልዩ ልዩ አቀራረጽ በልዩ ልዩ ሥራ ተሠርቶ የሚታየውን በየሥዕሉ ማሳየት።

  • ቀራንዮ መስቀል በቀራንዮ ክርስቶስ የተሰቀለበት ዋነኛው የቀራንዮ መስቀል።

  • ቀርነ በግዕዝ መስቀል እንደ በግ ቀንድ ኹኖ በተሠራው መስቀል በመጽሐፍ ድጕሰት ላይ የሚታይ ቆለፍ ቆለፍ ያለ።

  • ትእምርተ መስቀል የመስቀል ምልክት ወይም መስቀልኛ።

  • ነገረ መስቀል የመስቀልን ነገር መነጋገር መሥራት ማሳየት።

  • ዕርባን ሥራ መስቀል ብሩ ወርቁ በልዩ ልዩ አቀራረጽና ንቅስ ተነቅሶ በሙሻ ዘርየሚሠራ ዕርባን ሥራ ንቅስ መስቀል።

  • ዕርፈ መስቀል ማንካ ቀሳውስት ለሚቆርቡ ምዕመናን ደሙን የሚያቀብሉበት ማንካ በቤተ ክርስቲያን የሚኖር ዕርፈ መስቀል ይባላል።

  • የመስቀል አበባ በዘመነ ጽጌ የሚፈነዳው አበባ እንደ መስቀል ቅርጽና መልክ ያለው የመስቀል አበባ ይባላል።

  • የመስቀል ዎፍ ጥቍር ሰማያዊ የምትመስል በመስከረም በመስቀል በዐል ብቅ የምትል ድንቢጥ የመስከረም ዎፍ ትባላለች።

  • የመስቀል ደመራ በመስከረም ፲፮ ቀን ለመስቀል ዋዜማ ሕዝብ ኹሉ ርጥብ ዕንጨትን እያመጣ የሚደምረው ደመራ።

  • የመስቀል ጥቢ የመስከረም መስቀል ዘመን መስቀል ከዋለ በኋላ መስቀል ጥቢ መባል (ሰቀለ ሰቀለ መስቀል (<ግዕዝ>)።

  • የመስከረም መስቀል እሌኒ ንግሥት በመስከረም አስጀምራ ያስቆፈረችው በመስከረም ዐሥራ ሰባት ቀን የሚውለው በዐል ነው።

  • የመጋቢት መስቀል በመጋቢት ዐሥር ቀን የሚውለው የመስቀል በዐል ነው።

  • የሰሎሞን መስቀል የሰሎሞን የሊሻኑ ዐይነት መስቀል።

  • የስቅለት ማግስት ከስቅለት በማግስት የሚውለው ቅዳሜ ሹር።

  • የስቅለት ዕለት ክርስቶስ የተሰቀለበት መስቀል።

  • የተመሰቃቀለ መንገድ ዐራት ወገን ዐምስት ወገን ስድስት ወገን የሚያስኬድ አቋራጭ መንገድ።

  • የዐላማ መስቀል ለሃይማኖት ምልክት በዐላማ ላይ ለሚሰፋ የመስቀል ምልክት ወይም በሰንደቁ ላይ የሚታየው የዐላማ መስቀል።

  • የአንገት መስቀል እንደ ዕርባን ሥራ ወይም ልዩ ልዩ ሥራ ኹኖ ለአንገት እንዳይከብድ ትንሽ ኹኖ የሚሠራ መስቀል።

  • የዐጤ መስቀል በመስከረም ዐሥር ቀን ካህናት በቤተ መንግሥት ተሰብስበው ርእዩ ዘገብረ እግዚእነን ... አመልጥነው ተቀጸል ጽጌ እገሌ ሐፄጌ (ኅይለ ሥላሴ ሐፄጌ) እያሉ ወይም በእየ ጊዜው የነገሠዉን ንጉሥ የሚያወድሱበት ቀን ያጤ መስቀል ይባላል።

  • የእጅ መስቀል ጳጳሳት ኤጲስ ቆጶሳት ቀሳውስት በእጃቸው አዘውትረው የሚይዙት መስቀል።

  • ፀዋትወ መስቀል (<ግዕዝ>) ከመስቀል ወገን የኾነ መከራ ወይም የተቀደሱ የመስቀል ዕቆች።

_______

_______

 
 
 

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page