top of page

ሕዝብ ጀግና ይወዳል፣ እውነተኛ ጀግና ናፍቆናል ስለ ጽዮን ዝም አትበሉ! ተሟገቱላት! ሙቱላት!


https://youtu.be/a_dKv2Ht_fI

😇 ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል ❖ ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት ❖ መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም

🧕 "ስለ ጽዮን ዝም አልልም" <ኢሳ ፷፪፥፩>ኢሳ ፷፪፥፩>

ይህንን የተናገረው ልዑለ ቃል ኢሳይያስ እግዚአብሔር የራቀውን አቅርቦለት የረቀቀውን አጉልቶለት ትንቢት በሚናገርበት ዘመን ሲሆን ጽዮን የሚለው ስም እንደአገባቡ ይፈታል። ጽዮን የሚለው ቃል ኢየሩሳሌም ቤተክርስቲያን መንግስተ ሰማያት ወይም ድንግል ማርያም ቤተመቅደስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል፣ ኢየሩሳሌም ቤተእስራኤል (ቤተ ያዕቆብ) ቤተ መቅደስ ተብሎ የሚፈታበት ጊዜ አለ፣ በሌላ ሥፍራ ደግሞ የቃሉ አገባብ ኢየሩሳሌም ድንግል ማርያም ወይም መስቀል ክርስቶስ ተብሎ ሊተረጎም ይችላል።

  • ፩ኛ) ወደ ጽዮን ተራራና ወደ ሕይው እግዚአብሔር ከተማ ደርሳችኋል

  • ፪ኛ) ጽዮን የሚለው ቤተመቅደስን ነው

  • ፫ኛ) ጽዮን የሚለው ቃል የሚያመለክተው ክርስቶስ ስለተሰቀለበት ዕፀ መስቀል ነው

  • ፬ኛ) የቃል ኪዳኑን ታቦት ጽዮን ይለዋል

  • ፭ኛ) "አቤቱ ስለፍርድህ ጽዮን ሰምታ ደስ አላት"

  • ፮ኛ) ጽዮን የተባለችው ድንግል ማርያም ናት

ሰው ሁሉ እናታችን ጽዮን ይላል በውስጧም ሰው ተወለደ (መዝ ፹፮᎓፭)"እንዲል ቅዱስ ዳዊት የአዳም ዘር ሁሉ እናታችን እመቤታችን እያለ ያመሰግናታል።

🧕 ሕዳር ፳፩/21 | ዕግትዋ ለጽዮን | ጽዮንን ከበቧት | ስለ ጽዮን ዝም አልልም!

Posted by addisethiopia / አዲስ ኢትዮጵያ on November 30, 2021

https://youtu.be/I9kaOT6r90I

https://wp.me/piMJL-7xK

_______

_______

 
 
 

Recent Posts

See All

Comments


bottom of page