top of page

Turkish Airlines Pilot Suddenly Dies During Flight From US Forcing Emergency Landing


https://rumble.com/v5i61wq-turkish-airlines-pilot-suddenly-dies-during-flight-from-us-forcing-emergenc.html

✈ የቱርክ አየር መንገድ ፓይለት በረራ ላይ ሳለ ሕይወቱ አለፈ

ከአሜሪካ ወደ ቱርክ ሲጓዝ የነበረ የመንገደኞችን አውሮፕላን እያበረረ የነበረ ቱርካዊ ፓይለት በበረራ ላይ ሳለ ታሞ ሕይወቱ አለፈ። ፓይለቱ ከአሜሪካዋ ሲያትል ወደ ቱርኳ ኢስታንቡል በረራ ላይ በነበረበት ወቅት ነው አየር ላይ ሕይወቱ ያለፈው።

የ59 ዓመቱ ካፒቴን ኢልሺን ፔህሊቫን አውሮፕላኑን እያበረረ በነበረበት ወቅት ራሱን በመሳቱ ሁለተኛው ፓይለት እና ረዳት አብራሪው አውሮፕላኑን መቆጣጠራቸውን የአየር መንገዱ ቃል አቀባይ በኤክስ ገጻቸው ገልጸዋል።

“በአውሮፕላኑ ውስጥ ለፓይለቱ የመጀመሪያ እርዳታ ቢደረግለትም ሳይሳካ ቀርቷል። የአውሮፕላኑ አብራሪዎች በድንገተኛ ሁኔታ ለማረፍ ጥረት ቢያደርጉም ፓይለቱ በአየር ላይ እያለ ሕይወቱ አልፏል” ሲሉ ያህያ ኡስተን ገልጸዋል።

የቱርኩ አየር መንገድ ንብረት የሆነው ኤርባስ ኤ 350 አውሮፕላን ኒው ዮርክ ላይ እንዲያርፍ የተደረገ ሲሆን፣ ከዚያም መንገደኞቹን ወደ ቱርክ ለማብረር ዕቅድ ተይዞ እንደነበር ቃል አቀባዩ አክለዋል።

የበረራ ቁጥር ቲኬ 204 የሆነው አውሮፕላን ከሲያትል የተነሳው በአገሬው ሰዓት አቆጣጠር ማክሰኞ ምሽት 1 ሰዓት አካባቢ ነበር።

አብራሪው በካናዳዋ ግዛት ኑናቩት ህመም ማጋጠሙን ተከትሎ ባልደረቦቹ አውሮፕላኑን ተረክበው ወደ ጆን ኤፍ ኬኔዲ አየር ማረፊያ አቅንተዋል።

😮 ዋው! በትናንትናው ዕለት አውሎ ንፋስ ሚልተን የአሜሪካዋን ግዛት ፍሎሪዳን ለማጥቃት በደረሰበት ወቅት ሲ.ኤን.ኤን የሚያቀርበውን የቀጥታ ሥርጭት እየተከታተልኩ ነበር። ታዲያ በፕሮግራሙ መሃል ላይ አንድ 'የቱርክ ዓየር መንገድ' ማስታውቂያ ሲያቀርብ እራሴን የጠየቅኩት፤ "ለምንድን ነው ሲ.ኤን.ኤን ይህን ያህል ለቱርኮች እና አረቦች ይህን ያህል ለማስተዋወቅ የፈለገው? የቱርክ አየር መንገድ ለረጅም ጊዜ ከ CNN ጋር ልዩ ስፖንሰር ማድረግ እንዴት ጀመረ? የተሻለ ክፍያ የሚከፍሉ ሌሎች ስፖንሰሮችን ለማግኘት በእርግጥ ችግር ኖሮባቸው ነውን? እውነት በተሻለ መልክ ሊከፍሉት የሚችሉ ተቋማትን ሳያገኝ ቀርቶ?” የሚለውን ጥያቄ ነበር። አሁን ይህ…ዋው!

✈ A Turkish Airlines flight made an emergency landing at New York’s Kennedy Airport early Wednesday after the captain died onboard, airline officials said.

The Airbus A350-900 was heading from Seattle to Istanbul, Turkey when it made an extreme turn toward the Big Apple.

The 59-year-old pilot, identified as Ilcehin Pehlivan, “collapsed” during the flight, airline spokesman Yahya Ustun wrote on X.

“After an unsuccessful attempt to give first aid, the flight crew of another pilot and a co-pilot decided to make an emergency landing, but he died before landing,” the spokesperson said.

😮 Wow! Yesterday, I was watching CNN's live coverage of Hurricane Milton when it hit the US state of Florida. So, in the middle of the program, when a 'Turkish Airlines' commercial/ announcement was made, I asked myself; "Why does CNN want to advertise so much to Turks and Arabs? How could Turkish Airlines embark on exclusive sponsorship with CNN for such a long time? Do they really have difficulties in finding other sponsors that could pay them better?"

Now this....wow!

_______

_______

Comments


bottom of page