Miracle of St. Gabriel of Georgia & The Blooded Cross on The Girl’s Forehead
- Abraham Enoch
- Dec 29, 2024
- 3 min read
https://rumble.com/v63x8hy-miracle-of-st.-gabriel-of-georgia-and-the-blooded-cross-on-the-girls-forehe.html
😇 ገብርኤል 🧕 ማርያም ❖ ኡራኤል ❖ ጊዮርጊስ ❖ ተክለ ሐይማኖት ❖ መርቆርዮስ ❖ ዮሴፍ ❖ መድኃኔ ዓለም
😇 የጆርጂያ የቅዱስ ገብርኤል ተአምር እና በልጅቷ ግንባር ላይ ያለ የደም መስቀል ♱
የሃገረ ጆርጂያ ኦርቶዶክስ ቅዱስ አባት ከሆኑት ከቅዱስ ገብርኤል (ኡርጌባዜ) ከርቤ ከሚፈስበት ስዕል ብዙ ተአምራት እየታዩ ነው።
በጆርጂያ ብዙ አማኞች በተብሊሲ ከተማ ከሚገኝ ቤተሰብ የሆነው “ሞኙ ለክርስቶስ” ከሚለው የቅዱስ ገብርኤል ምስል ከርቤ በሚፈስስበት ተአምር እየተደነቁ እና እየተደሰቱ ነው። በሩስታቪ 2 የቴሌቭዥን ጣቢያ ላይ ያለው የ"ፖስትስክሪፕት" ፕሮግራም እንደሚለው ከዚህ ስዕል ብዙ ሰዎች ተፈውሰዋል።
በዚህ ሥዕል ላይ ተአምራዊ ፈውሶች በተከታታይ እየተከሰቱ ነው። ዜናውም በመላው አለም እየተሰራጨ ሲሆን ብዙ አማኞች ቅርሱን ለማክበር ወደ ቤተሰባቸው እየጎረፉ ሲሆን ልዩ ጊዜም ተሰጥቷቸዋል።
ከነሱ መካከል ሊካ አሊምባራሽቪሊ እና ኢሪና ማይሱራድዜ ይገኙበታል። በቅዱስ ገብርኤል ሥዕል ፊት ከጸለዩ እና ከተቀቡ በኋላ ወደ ቤታቸው ተመለሱ።
ሲመለሱ በልጅቷ ግንባር ላይ ያለው ከርቤ ቀይ ሆነ። የእነዚህን ተዓምራት ሁሉ ምስሎች በካሜራዎቻቸው ሠርተዋል። ተአምራቱ ግን በዚህ አላበቁም። ወደ ቅዱሱ አባት ገብርኤል መቃብር ላይ የቀረበችው ልጅ ልቧ ላይ ከያዘችው አማሌት ደም ማፍሰስ ጀመረ።
ለሁለት ቀናት ያህል ደም የሚመስል ፈሳሽ ከአማሌቱ ከምድር ጋር ፈሰሰ እና ለሁለት ቀናት ደግሞ ቀለም የሌለው ፈሳሽ ታየ። ልጃገረዷ ቀደም ሲል ብዙ በልብ ሕመም ትሠቃይ ነበር። ከእናቷ ጋር የቅዱስ ገብርኤልን ንዋያተ ቅድሳትን ሊያከብሩ ሄዱ በዚያም ጉብኝት ቅዱሱ ራሳቸው ለእናቲቱ ተገልጠው ባርኳትና ስለ ምንም ነገር እንዳትጨነቅና ሁሉም ነገር መልካም እንደሚሆንላቸው ነግረዋቸው ነበር። ፈሳሹ ከምድር ጋር ከአማሌቱ የፈሰሰበት ልብስ ለሳይንሳዊ ምርመራ እና ለባለሙያዎች ምርመራ ተልኳል። የፈተና ውጤቱ ይፋ ይሆናል።
በተጨማሪ ሦስት ዲዳዎች ከርቤ ከተቀቡ በኋላ መናገር መጀመራቸውም ተነግሯል።
በእውነት ድንቅ ነው!
ከዚህ ቀደም አውስቼው ነበር፤ ከጥቂት ዓመታት በፊት በቅዱስ ሚካኤል ዕለት አዲስ አበባ በሚገኘው ቦሌ ቅዱስ ሚካኤል ቤተ ክርስቲያን ግቢ በሚገኘው አንድ ውብ ቦታ ላይ ቁጭ ብየ ነበር። እዚያም አንዲት የሃያ ዓመት ገደማ የሚሆናት እኅት አጠገቤ መጥታ ቁጭ አለች። ስለ ክብረ በዓሉ ማውራት ስንጀምር ልክ ይህች ጆርጂያዊት እኅታችን ግንባር ላይ የሚታየው ዓይነት መስቀል በአዲስ አበባዋ እኅታችንም ላይ ታይቶኝ ምን እንደሆነ ስጠይቃት በፈገግታ፤ “እንዲሁ ነው! ማዲያት ነገር ነው፤ ንቅሳት አይደለም።” አለችኝ። ከአክሱም እንደመጣች ነገረቸኝ፤ እኔም ፎቶ እንዳነሳ ጠይቄ አነሳሁት።። አዎ! ንቅሳት አልነበረም፤ ግን ቀለሙ ደማማ ወይንም ቀይ አይመስለኝም። ፎቶዎን ፈልጌ አቀርበዋለሁ!
😇 In Georgia miracles are occurring from the myrrh-streaming Icon of St. Gabriel (Urgebadze)
In Georgia many believers are rejoicing at the miracles occurring from the myrrh-streaming icon of Blessed Gabriel, “the Fool-for-Christ”, that belongs to a family in Tbilisi. Numerous people have been healed from this icon, as relates the “Postscript” program on the Rustavi 2 TV channel.
The icon of St. Gabriel First began streaming myrrh seven months ago. It was shown to Catholicos-Patriarch Ilia II who confirmed this.
Over the last two months, twelve more icons and photographs of elder Gabriel began shedding myrrh in the family which possesses this relic.
And in January another, a larger Icon of Father Gabriel began shedding myrrh abundantly.
Maka, the keeper of this icon, relates: “Fr. Gabriel appeared to me, looking as he is seen on icons, saying: “Has anyone already told you anything?” I answered: “No”. Then he replied: “Then I will come once more.” The next morning, as I went out of my bedroom, I saw that all other Icons of St. Gabriel were covered with myrrh. So I realized why Fr. Gabriel had told me he would return again: his return was through the shedding of myrrh.”
St. Gabriel said to her: “I have chosen you because the grace of God is upon you. And the people whom you will anoint with this myrrh will be healed.” The Church representatives blessed Maka to anoint those flocking to venerate the holy icon with this myrrh.
Miraculous healings are occurring at this icon. The news of this is being spread throughout and crowds of faithful are flocking to the family to venerate the relic and a special time is allotted for them.
Among them there are Lika Alimbarashvili and Irina Maisuradze. After praying before the holy Icon of Venerable Gabriel and anointing they came back home.
Upon their return the myrrh on the girl’s forehead became red. They made photographs of all this. But the miracles did not end with this. An small case with earth from the elder Gabriel’s grave, attached near the girl’s heart, began shedding blood as well.
For two days a liquid, resembling blood, poured from the amulet with earth, and for another two days, some colorless liquid. The girl formerly suffered much from a heart disease. With her mother they went to venerate the Relics of St. Gabriel and during that visit the saint himself appeared to the mother, blessed her and said that she should not worry about anything and that everything would be well with them. The clothes on which the liquid had poured from the amulet with earth, was sent for a scientific investigation and expert examination. The examination results will be announced.
It has also been reported that three dumb people began to speak after anointing with the myrrh.
_______
_______




Comments