Happy Epiphany -- እንኳን ለብርሃነ ጥምቀቱ በሰላም አደረሰን!Abraham EnochJan 18, 20132 min readሌላ ጊዜ የምመለስበት፡ ወቅታዊና አንገብጋቢ አጭር የጥምቀት መልዕክት፡አገር ቤት ያላችሁ ታታሪ መንፈሳውያን መሪዎች፣ አባቶች፤ ባካችሁ ቅድስት አገራችንን ለቃችሁ (ለስብሰባም ቢሆን)፡ በተለይ ወደ ሰሜን አሜሪካ መሄዱን አቁሙ ውጭ ያላችሁ ታታሪ ኢትዮጵያውያን መንፈሳዊ መሪዎችና አባቶች ባላችሁበት ቦታ የወንጌል ሰባኪነትን ሥራ የማትሠሩ ወይም የተዋሕዶ ክርስትናንን ለአገሬው የማታስተዋውቁና ተመሳሳይ ኃላፊነት የሌላችሁ ከሆነ፡ ባካችሁ ወደ አገራችሁ ቶሎ ተመልሳችሁ ነፍሳችሁን ከአውሬው ወጥመድ አድኑበውሀበመንፈስ ቅዱስበሥቃይመጠመቅ ነው። (ሉቃ. 3፥16፣ 12፥50)የዮሐንስ ጥምቀት ወደፊት የሚመጣውን ያመለክት ነበር (ማቴ. 3፥11-12)--የክርስቲያን ጥምቀት የተፈጸመውን የክርስቶስን የአዳኝነት ሥራ ያሳስባል (ሮሜ. 6፥3-4)--የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት በበዓለ 50 ዕለት በቤተ ክርስቲያን ተደረገ (የሐዋ. 1፥5፣ 2፥1-4)ከዚያ ጊዜ ጀምሮ ምእመናን ሁሉ አንድ አካል እንዲሆኑ በመንፈስ ይጠመቃሉ። (1ቆሮ. 12፥13) “እለ ጥሙቃን በመንፈስ ቅዱስ" (ቀሌምንጦስ)ክርስቶስ ሲጠመቅ መንፈስ ቅዱስ መውረዱ ለእኛ ጥምቀት ምስጢር ማስረጃ ነው። (ሉቃ. 3፥21-22፣ የሐዋ. 2፥38፣ ቲቶ. 3፥5)የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የውሀን ጥምቀት ሊከተል ይችላል። (ዮሐ. 8፥4-17፣ 10፥44-48)ጥምቀት ከክርስቶስ ጋር አንድ ያደርገናልና በዚህ መሠረት ከኅጢአት እንደ ተለየን ቈጥረን በአዲስ ሕይወት እንኖራለን (ሮሜ. 6፥1-11) የመጽሐፍ ቅዱስ መዝገበ ቃላት ገጽ 245 ተመልከት።ጌታ እየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀበት ዋና ምክንያት፦በጥምቀቱ ጥምቀተ ክርስትናን ሊመሠርትልንውሀውን ሊባርክልንና ሊቀድስልንከእግዚአብሔር የመወለድን ጸጋ ሊያድለንስርየተ ኅጢአትን ሊሰጠንጽድቀ ተስብኦንና ትንቢተ ነቢያትን ሊፈጽምነው።ዛሬ በቤተ ክርስቲያን በሚፈጸመው ምስጢረ ጥምቀት አማካኝነት ከጌታ ጐን በፈሰሰው ማየ ገቦ ተጠምቀን ከኅጢአትና ከመርገም እንድናለን። ማንም ሰው ሳይጠመቅ የሠራው ኅጢአት የሚሠረይለት በጥመቀት ነው። ሁለተኛም በጥምቀት ከእግዚአብሔር ይወለዳል።በዓለ ጥምቀትጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የተጠመቀው ጥር ፲፩ ቀን ከሌሊቱ ፲ ሰዓት ላይ ነው። በዓለ ጥምቀት በልሳነ ዮናኒ ወይም በግሪክኛ ቋንቋ ኤጲፋኒያ (Epiphania) ይባላል። ኤጲፋኒያ ማለት አስተርእዮ (መገለጥ) ማለት ነው። ምክኒያቱም በዚህ ዕለት ምሥጢረ ሥላሴ ስለ ተገለጠ ነው። "አብ በሰማይ ሆኖ ይህ የምወድደው ልጄ ነው፤" ብሎ መሰከረ። ወልድም በዮርዳኖስ ወንዝ ቆሞ በዮሐንስ ሲጠመቅ ታየ፤ መንፈስ ቅዱስ በነጭ ርግብ አምሳል በወልድ ራስ ላይ ተቀምጦ ታየ።ለዚህም መጥምቁ ዮሐንስና ወንጌላውያን ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በተጠመቀና ከውሀው በወጣ ጊዜ ያን ጊዜ ሰማይ ተከፈተ፤ መንፈስ ቅዱስም በርግብ አምሳል ወርዶ በላዩ ላይ ተቀመጠ፤ ቃልም ከሰማይ መጣ፤ "ይህ የምወድደው ልጄ ነው" ብሎ መስክሩዋል በዚች ዕለትም ጌታችን ራሱን ገልጦአል፤ ከዚህ በፊት ሠላሳ ዓመት ያህል ራሱን አልገለጠም ነበር፡ ግን በዚች ዕለት ለእስራኤል ልጆች ራሱን ገለጠ። "እነሆ የዓለምን ኅጢአት የሚያስወግድ የእግዚአብሔር በግ" ብሎ ዮሐንስ እንደ መሰከረ ለምሥዋዕት ቀረበ "እኔ አላውቀውም ነበር። ነገር ግን እስራኤል ያውቁት ዘንድ በውኃ ላጠምቅ ስለዚህ መጣሁ" አለ ዮሐንስ።ዮሐንስ ክርስቶስን ከእስራኤል ጋር በማስተዋወቅ ያጠምቅ እንደነበረ እኛም አምላክነቱን፥ መድኅኒትነቱን ከአይሁድና ከተንባላት፥ ከአሕዛብና ከአረማውያን ጋር ለማስተዋወቅ ወንጌልን እንስበክ፥ ጥምቀተ-ክርስትናንም እናጥምቅ፣ ምስጋና ለእግዚአብሔር!__
Fire at The Church of Saint Mary The Virgin in Luxor Egypt – Huge Explosion Inside the Church ባለፈው ቅዳሜ ዕለት (ዮሐንስ እና ማርቆስ) በ ግብፅ ሉክሶር/ቴቤን የድንግል ማርያም ቤተክርስቲያን ላይ የደረሰ የእሳት አደጋ ፥ በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ከፍተኛ ፍንዳታ ነበር
Comments