CNN Embarrassment – Bombshell pic PROVED Rescued Syrian ‘Prisoner’ Was Assad Officer
- Abraham Enoch
- Dec 19, 2024
- 2 min read
https://rumble.com/v60vrct-cnn-embarrassment-bombshell-pic-proved-rescued-syrian-prisoner-was-assad-of.html
🎤 የ CNN አሳፋሪ ተግባር – ሃሰተኛው ዝነኛ ፎቶ ተረጋገጠ፤ 'ድኗል' ተብሎ በቴሌቪዥኑ የታየው የሶሪያ 'እስረኛ' የአሳድ መኮንን ነበር
ለጋዜጠኝነት ሌላ ጉዳት። ሲ ኤን ኤን ባለፈው ሳምንት ላይ ቀደም ሲል በኢራቅ እና ሊቢያ ሲያደርግ እንደነበረው የወቅቱን ዋና ዜና ይዞ በመምጣት፤ 'በሶሪያ የአሳድ አገዛዝ የእስር ስቃይ ሰለባ የሆነው አንደ ሰው ከእስር ሲፈታ ነው' የሚል ቲያትር ሠርቶ ነበር። የዜና ጣቢያው በሀሰት ባቅነባበረው ድራማ፤ "ሰውየው ብዙ ወራት በእስር ቤት ውስጥ ብዙ ቀናት ሳይበላ እና ሳይጠጣ ወጣ።" ጋዜጠኛ ክላሪሳ ዋርድ ሃሰተኛ ዘገባ አቅርባ ነበር።
ይህም 'በድንገት' በሲ.ኤን.ኤን በሽፋን እንደተገኘ አድርጋ በመዘገብ ምስሎቹ በዓለም ዙሪያ ተልከው ነበር። ከመጀመሪያው ጀምሮ በማህበራዊ አውታረመረቦች በኩል ብዙ ሰዎች የዚህን ዝግጅት ትክክለኛነት በመጠራጠራቸው የሲ.ኤን.ኤን መሠሪዎች በመጀመሪያ "በሴራ" ተከሰው ነበር። የአሜሪካ ሚዲያዎች ይህን ሰው በድብቅ እስር ቤት ውስጥ እንደሌላው የአሳድ መንግስት ሰለባ አድርገው በተደጋጋሚ አቅርበውት ነበር። ይህ ሃሰተኛ ድራማ ግን ተጋልጦ እውነታው አሁን ታውቋል። ሰውየው በፍጹም እስረኛ አልነበረም፤ ሰውየው የአሳድ አገልጋይ የነበረ መኮንን ነው። ለ፳/20 ዓመታት በዓለም ዙሪያ በተለይ በአረቡ ዓለም እየተዘዋወረች የምትዘግበዋ ክላሪሳ ዋርድ አሁን በውርደት እሳት ተጠምቃለች።
ግን እንዴት ያለ ነውር/ቅሌት ነው፤ ጃል! ቅሌታሞች! ግብዞች! በሰሜን ኢትዮጵያ፣ በሳዊዲ አረቢያ፣ በተባበሩት አረብ ኤሚራቶች እየተጨፈጨፉ በጅምላ ስለሚቀበሩት ኢትዮጵያውያን፣ በመላው የዓረብ ዓለም በባርነት እና በየእስር ቤቱ ስለሚሰቃዩት ተገን ፈላጊዎች እና የቀን ሠራተኞች እነ ሲ.ኤን.ኤን ክልባቸው ሲዘግቡ አይታዩም/አይሰሙም።
💭 A BOMBSHELL image of the viral Syrian "prisoner" discovered by CNN crew proves he was actually one of Assad's ruthless officers.
The bogus inmate was found trembling under a blanket before being freed by the team, exclaiming: "Oh God, there is light."
The man named himself to CNN's Clarissa Ward as Adel Gharbal, a father from Homs.
But, following claims by the fact-checking site Verify-Sy that he could be one of Assad's puppets, CNN launched an investigation into the man's identity.
The broadcaster soon confirmed that the man was not called Adel Gharbals - but Salama Mohammad Salama.
Salama "was known by locals for running the Air Force Intelligence Directorate's checkpoints" and was accused of "having a reputation for extortion and harassment," CNN said.
_______
_______




Comments